በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ለተማሪዎች የክረምት ወራት ስልጠና እየተሰጠ እንደሆነ ተገለፀ።

ነሀሴ 19/2017ዓ.ም[ወልቂጤ]

በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ለተማሪዎች የክረምት ወራት ስልጠና እየተሰጠ እንደሆነ ተገለፀ።

ነሀሴ 19/2017ዓ.ም[ወልቂጤ]

ከኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት አማካኝነት በስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ዘርፍ ልዩ ተሰጥኦና ዝንባሌ ያላቸውን ታዳጊ ሕፃናት የበለጠ ለማብቃት ራዕይ በመሰነቅ በተለያዩ ፕሮግራሞቹ በአስትሮኖሚ፣ ስፔስ ሳይንስ፣ የጂኦግራፊ መረጃ ስርዓት (ጂአይኤስ) ; ሪሞት ሴንሲንግን ጨምሮ በተለያዩ መስኮች ስልጠናው በቴክኖሎጂ በመታገዝ ልዩ ፍላጎትና ብቃት ያላቸውን ታዳጊዎች በተለያዩ የሥልጠና ማዕከል አድርጎ ስልጠናው እየወሰዱ እንደሚገኙ የወልቂጤ ከተማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሀምዱ ካሚል ገልጸዋል።

በስልጠናው ልዩ ዝንባሌ ያላቸውን ተማሪዎች ነገን ታሳቢ ያደረገ ትጋት በመሆኑን በዘርፉ የሀገራችንን ስም የሚያስጠሩ ተመራማሪዎችን የማፍራት አላማም ያለው እና ውጤትም እየተመዘገበበት እንደሆነም ለአብነት ነቢሀ ነስሩ ማሳያችን ነች ሲሉ ተናግረዋል።

በቴክኖሎጂው ዘርፍ እነዚህ ተሰጥኦ ያላቸው ሀገር ተረካቢ ትውልዶችን ዘመኑ የደረሰበትን የቴክኖሎጂ ጎዳና አብሮ በማራመድ በሀገር ብሎም በከተማው ላይ ዘመናዊ የአሰራር ስርዓት በማበልፀግ ከተለያዩ ስርቆቶች ነጻና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል መሆኑንም ሀላፊው ገልጸዋል ።

ስልጠናውን ሲሰጡ ያገኘናቸው ሰርቬ መምህር ደጀኔ አምሳሉ በበኩላቸው ስልጠናው ጂኦስፓሻልእና ስፔስ ሳይንስ ላይ የሚሰጠው ስልጠና በፈጠራው ዘርፍ ላይ ልዩ ዝንባሌ ያላቸው ተማሪዎች ተጨማሪ እውቀትን አዳብረው በቴክኖሎጂው ዘርፍ ስለተለያዩ ነገሮች ትንተና መስጠት እንዲችሉ ያግዛቸዋል ብለዋል።

በዚህ ትምህርት መስክ ባገኙት እድል በሚገባ ትምህርቱን በመከታተል ተሰጥኦአቸውን ፈልገው በማግኘት ለነገ ህይወታቸው የተሻለ መሰረት እንዲይዙ ጥሪያቸውን አቅርበዋል ።

በስልጠናው ሲሳተፉ ያገኘናቸው ተማሪ ሶኒ ሀይሌ ና አብድልቃይር አብድልካፍ እንደገለጹት ጂኦስፓሻልና ስፔስ ሳይንስ ላይ በሚወስዱት ስልጠና በመታገዝ የጀመሯቸው የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ ለሀገር ብሎም ለከተማቸው ዘመናዊ አሰራር ስርዓትን ለማስፈን እንደሚሰሩም ተናግረዋል።

Previous “ጽዱ ከተማን ለመፍጠር በየሳምንቱ የተጠናከረ የጽዳት ዘመቻ ስራ እያከናወንን እንገኛለን፦ አቶ ሙራድ ከድር የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ

Leave Your Comment

የቋንቋ አማራጭ

🇺🇸 English
🇪🇹 አማርኛ
🇪🇹 Afan Oromo