
ሀምሌ1/2017ዓ.ም [ወልቂጤ ]
በወልቂጤ ከተማ አስተዳደር የ2017ዓ.ም አመታዊ ግብር መክፈያ መርሀግብር ተካሄደ።
የወልቂጤ ከተማ ገቢዎች ፅህፈት ቤት ከሐምሌ 1 እስከ_ሐምሌ 5 የ2017 ዓመተ ምህረት አመታት ግብር ” ግብራቸውን በወቅቱ የሚከፍሉ ግብር ከፋዮች ብልሆች ናቸው” በሚል መሪ ቃል ይፋዊ ማስጀመሪያ አካሄደ።
በማስጀመሪያ መርሀ-ግብር ላይ የተገኙት የማእከላዊ ኢትዮጵያዊ ክልል ገቢዮች ቢሮ ምክት ሀላፊ እና የታክሰር ህግ ማስከበር ዘርፍ ሀላፊ አቶ ሰለሞን ውድነህ እንደተናገሩት እንደሀገር ገቢ ሰብስበን በየደረጃ የሚነሱ የልማት ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት መንግስት በገቢ አሰባሰብ ስራ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
እንደ ክልል ከ20.3 ቢሊዮን እቅድ በማቀድ ወደ 16.2 ቢሊዮን መሰብሰብ መቻሉን የገለፁት አቶ ሰለሞን ውድነህ የነጋዴው ማህበረሰብ ግብር በአግባቡ በታማኝነት በመክፈል ለልማትና ለዕድገት ያለውን ተሳትፎ ያሳየበት መሆኑን ገልፀዋል ።
በበጀት አመቱ በያዝነው እቅድ መሰረት የጀመርናቸው ትላልቅ ፕሮጀክቶች በወቅቱ ለማጠናቀቅ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ በአግባቡ ግብር በመክፈል የዜግነት ግዴታችንን ልንወጣ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።

የጉራጌ ዞን ገቢዎች መምሪያ ሀላፊ አቶ ሚነውር ሀያቱ እንደተናገሩት የወልቂጤ ከተማን እድገትና ልማት ለማረጋገጥ ሁሉም የከተማው ነዋሪ አሻራቸውን ሊያሳርፍ ይገባል ብለዋል።
የነጋዴው ማህበረሰብ በአለው አቅም በገቢው መጠን የህዝቡን የልማት ጥያቄ ለመመለስ በአግባቡ ግብር መክፈል ይጠበቅበታል ሲሉ ተናግረዋል።

ግብር የሁሉም ነገር መሰረት ነው ያሉት የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሙራድ ከድር ለልማትና የመልካም ጥያቄ፣ለፖለቲካ እንዲሁም ለኢኮኖሚ ቁልፍ ጉዳዮች መሠረት ነው ብለዋል።
እንደከተማችን የተጀመሩና ያደሩ ትላልቅ ፕሮጀክቶች ለማጠናቀቅ የከተማው የነጋዴው ማህበረሰብና ነዋሪ ከአመራሩ ጋር በቅንጅት እየሰራ ይገኛል።
እእንዲሁም ወልቂጤ ከተማ በእድሜዋ ልክ ያላትን ሀብት በአግባቡ ተጠቅመን ህዝቦቿንና ነዋሪዎች የምትመሰል ያደገችና የበለፀገች ከተማ መፍጠር ይገባል ብለዋል።
ዛሬ የተጀመረው 2017 ዓ.ም የ “ሐ” የገቢ አሰባሰብ ከ25 ሚሊዮን ብር በላይ ለመሰብሰብ መታቀዱን አንስተው በተሳካ ሁኔታ ለማከናወን ሁላችንም ርብርብ ማድረግ ይጠበቅብናል።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሰፋ ዘይኑ እንደተናገሩት ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ እና በህዝቦችን የሚነሱ የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግር ምላሽ ለመስጠት አስተማማኝ የሀብት መሰረት አስፈላጊ በመሆኑ አስተማማኝ በዜጎች በታማኝነት የሚሰበሰብ ግብር ነው ብለዋል።
በበጀት አመቱ የነበሩ ጥንካሬዎች በማጠናከር በተስተዋሉ ድክመቶች በማረም የ2018 በጀት ዓመት በከተማችን የተጀመሩ የልማት ስራዎች መሰረት የምናሲዝበትና የምናሳድግበት ነው ብለዋል።
የደረጃ “ሐ” ግብር ግብር ከፋዮች በተቀመጠው የጊዜ ገደብ በተመረጡ ቦታዎች እና የኦንላይን ሲስተም በቴሌ ብር በወቅቱ በታማኝነት መክፈል ይገባል ሲሉ ተናግረዋል ።

በወቅቱ ተገኝተው ግብር ሲከፍሉ አግኝተን ካነጋገርናቸው ታማኝ ግብር ከፋዮች መካከል ከሰጡን አስተያየት ግብር መክፈል ለአንድ ሀገር ልማትና እድገት ያለውን አስተዋጽኦ በመገንዘብ በወቅቱ ግብር መክፈል ይገባል ብለዋል።
ቀጣይ ለከተማው ሁለንተናዊ እድገትና ለውጥ በሚያግዙ ተግባራት የበኩላቸውን እንደሚወጡ ገልፀው የከተማው የንግዱ ማህበረሰብ በወቅቱ ግብር መክፈል እንዳለበት ጠቁመዋል ።

