ያሉንን ደራሲያን አቅምና እውቀት ተጠቅመን ቋንቋችንን በማበልፀግ የህብረተሰቡ ታሪክ ፣ቋንቋ፣ባህል ፣እሴት ለትውልድ በማስተላለፍ የበኩላችንን ልንወጣ ይገባል ሲሉ ከንቲባው ተናግረዋል።
የጉራጌ ደራሲያንና ፀሃፋት ማህበር መመስረት የብሔርሰቡ ባህል፣ ቋንቋ ፣ ታሪክ እና ሌሎች እሴቶች እንዲተዋወቁና እንዲለሙ አስተዋጽኦው የጎላ መሆኑ ተገለፀ።

የጉራጌ ደራሲያንና ፀሃፋት ማህበር የምስረታ ጉባኤው አካሄደ ።
በምስረታ ጉባኤው በክብር እንግድነት የተገኙት የወልቂጤ ከተማ ከንቲባ አቶ ሙራድ ከድር ባስተላለፉት መልዕክት ሀገር የምትሰራው እና ትውልድ የሚቀረፀው በእውቀትና በጥበብ በመሆኑ ደራሲያን ትልቁን ድርሻ ይወስዳሉ ብለዋል።
ያሉንን ደራሲያን አቅምና እውቀት ተጠቅመን ቋንቋችንን በማበልፀግ የህብረተሰቡ ታሪክ ፣ቋንቋ፣ባህል ፣እሴት ለትውልድ በማስተላለፍ የበኩላችንን ልንወጣ ይገባል ሲሉ ከንቲባው ተናግረዋል።

የጉራጌ ማህበረሰብ አንድነት የሚያጠናክሩ የርስ በርስ ቅንጅታዊ ተግባራትን በማከናወን እየተማማርን በህብረተሰቡ ተቀባይነት ያለው ስራ መስራት እንደሚጠበቅ ገልፀው ከተማ አስተዳደር ባለው አቅምና ሀብት የበኩሉን እንደሚወጣም ጠቁመዋል ።
የማህበሩ አደራጅ ኮሚቴ የሆኑት ደራሲ ወንድሙ ብሩ እንደገለጹት የማህበሩ መመስረት ዋና አላማ የጉራጌ ህዝብ ታሪክ ፣ቋንቋና ባህል ፣እሴት ለተተኪው ትውልድ ለማሳወቅና እንዲያሳውቅ ለማስቻል ያለመ ነው ።
የማህበረሰቡ ማህበራዊ ፣ኢኮኖሚያዊ እሴቶች ተሰንደው በጥራትና በብዛት ለተተኪው ትውልድ በማስተላለፍ በተደራጀ መልኩ ህዝቡ የሚፈለገው ውጤት ማስመዝገብ ይገባል ብለዋለ።

ማህበሩ የጉራጌ ተወላጅ የሆነ በስፋት ለአንድ አላማ የሚሳተፍበት አንድነት የሚጠናከርበት ሲሆን ያሉን ደራሲያን እውቀታቸውን ለትውልድና ለህዝባቸው የሚያስተላልፉበት ነው እንደሆነም አክለዋል።
መንግስት ቋንቋና ባህል ለማሳደግ እያደረገ ያለው ጥረት ከፍተኛ ነው ያሉት ደራሲ ወንድሙ ማህበሩ የተሻለ ስራ እንዲሰራና የሚፈለገው ውጤት ለማምጣት ድጋፍና ክትትል እንዲያጠናከር ጠይቀዋል።
ረዳት ፕሮፌሰር ካሚል ኑረዲን የማህበሩ መመስረት አላማና የመተዳደሪያ ደንብ ሰነድ ባቀረቡት ወቅት በየትኛው ቋንቋ የተፃፈ የጉራጌ ማህበረሰብ ቋንቋ፣ታሪክ ፣በማህበራዊ ፣ኢኮኖሚያዊ እና ሌሎች እሴቶች ላይ የሚፃፉ ፁሁፎች ለማሳደግ መሆኑን ገልፀዋል።
የነጠረ የጠነከረ የተሻለና የበሰለ ፁሁፍ ለተደራሲያን ለማድረስ እና ታሪክ ተሰንዶ እንዲቆይ በእውቀት ላይ የተመሰረተ ስራ ለመስራት እንደሆነም አንስተዋል።

ማህበሩ ምስረታው ወልቂጤ ከተማ ማድረጉን ገልፀው የደራሲያን ማህበሩ አባላት በቀጣይ በሁሉም የጉራጌ አካባቢዎች እና ሌሎች ከተሞች ላይ የሚገኙ ስለ ጉራጌ ባህል ፣ ቋንቋ፣ ታሪክ እና እሴቶች በጉራጊኛ፣ በአማርኛና በእግሊዘኛ የሚጽፉ ደራሲያንና አማተር ፀሀፍት እንደሚያካትት ተገልጿል።
በጉራጊኛ ቋንቋ የተፃፉ ስድስት መፅሀፍት ለተደራሲያን ያበረከቱት ደራሲና ገጣሚ ክፍሌ ተመስገን እንደተናገሩት ማህበሩ መመስረቱ ለጉራጌ ማህበረሰብ ትልቅ ጠቀሜታ እንዳለው ገልፀው ቋንቋ ለማሳደግና አማተሮች ለማበረታታት ያግዛል ብለዋል።
ደራሲያን የማህበረሰቡ ታሪክ እንዳይጠፋና እንዳይዛባ መፅሀፍትን በመገምገም የጉራጌ ታሪክ ለተደራሲያን ተደራሽ እንዲሆን ያግዛል ።
ትውልዱ አንባቢ በመሆን ቋንቋና ታሪክ በማወቅ የጉራጌ ህዝብ አንድነት ከፍ የምናደርግበት በመሆኑ አባል በመሆን በእውቀት፣በሀሳብ እንዲሁም በጉልበት ማገዝ ይገባል ሲሉ ደራሲና ገጣሚ ክፍሌ ተመስገን ተናግረዋል።

ሚዲያዎች የተሰሩ ስራዎች ተደራሽ በማድረግ ትውልድን በማበረታታት የተሻ ስራ እንዲሰራ መደገፍ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
በመድረኩ የተገኙ አካላት እንደተናገሩት ማህበሩ መመስረቱ የጉራጌ ህዝብ ታሪክ፣ ቋንቋና ባህል እንዲሁም ሌሎች የማህበረሰቡ እሴት ለትውልድ ለማስተላለፍ ያለው ጠቀሜታ ከፍተኛ ነው ብለዋል።

አንድነታችንን በማጠናከር ሁሉም ባለው እውቀት ፣ገንዘብ እና ሀሳብ አጋዥ በመሆን ማህበሩ ለተቋቋመለት አላማ የበኩላችንን ልንወጣ ይገባል።
በመጨረሻም የማህበሩ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ምርጫ የተካሄደ ሲሆን በዚህም መሠረት:-
1.አቶ ወንድሙ ብሩ :-ሊቀመንበር/
2.ደራሲና ገጣሚ ክፍሌ ተመስገን :-ምክትል ሊቀመንበር
3. ረዳት ፕሮፌሰር ካሚል ኑረዲን :- ፀሀፊ
4.አቶ ክፍሌ አንሳ :- ሂሳብ ሹም
5.አቶ ቢንያም ሽመልስ :-የውስጥ ኦዲት
6.አቶ በሀሩ ሊላጋ :-ገንዘብ ያዥ
7.አቶ ዳኜ አሰፋ :- የንብረት ሃላፊ በመሆን የጉራጌ ደራሲያንና ፀሃፋት ማህበር አመራር ሆነው እንዲመሩ በመስራች አባላት በሙሉ ድምፅ ፀድቋል።


