አመራሩ ህዝብ የሚያነሳቸውን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ አሁንም በቁርጠኝነት አጠናክሮ ሊሰራ ይገባልም ብለዋል።

ሚያዚያ O3/2O17 ዓ/ም [ወልቂጤ]

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት የድህነት ቀናሽ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አመራር አባላት የባለፉት ዘጠኝ ወራት የስራ አፈፃፀሞችን ግምገማ አደረገ።

በፓርቲና በመንግስት ቅንጅት የሚፈጸሙ የንቅናቄ ተግባራት አፈጻጸም ግምገማና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችም ተቀምጧል።

በእለቱም የትራንስፎርሜሽን ሴክተሮች የ9ወራት እቅድ አፈጻጸም ያቀረቡ ሲሆን በከተማ አስተዳደሩ ብልጽግና ፓርቲ የርዕዮትና ፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ በሆኑት አቶ ጴጥሮስ አስራት የተጠቃለለ ሪፖርት የቀረበ ሲሆን በዋናነት

በከተማው ለሚከናወነው የኮሪደር ልማት ስራ ህብረተሰቡ የማሳተፉ ስራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ተገልጿል።

የአመራር አባላቱ ባለፉት ዘጠኝ ወራት የተከናወኑ ስራዎችን በጥልቀት የገመገሙ ሲሆን

በዚህም ባለፉት ዘጠኝ ወራት አመርቂ ተግባራት መከናወናቸውንና በድክመት የተለዩ ጉዳዮች ደግሞ በቀጣይ እንዲታረሙ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል።

ልማትን ለመስራት ገቢን በአግባቡ መሰብሰብ ወሳኝ መሆኑን በጥልቀት የገመገሙት የካቢኔ አባላቱ ያልተነኩ የገቢ አማራጮችን አቅማችን አሟጠን ና ስልት ነድፈን በመሰብሰብ የታቀዱ ልማቶችን ማሳካት እንደሚገባም ተወያይተዋል።

በጤናው ዘርፍ ለማህበረሰቡ የጤና መድህን ተጠቃሚ ለማድረግ በንቅናቄ የተሰራው ስራ የገቢ አቅማችን ለማሳደግም ነቸጀመረው ስራ መጠናከር እንዳለበት ተገልጿል ።

የትምህርት ስብራትን ለመጠገን፣ ስራ ዕድል ፈጠራ እና በከተማ ግብርና መስክ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ተጠቁሟል።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ታደለ በቀለ እንደገለፁት ባለፉት ዘጠኝ ወራት በርካታ የልማት ስራዎች ማሳካት መቻሉን ጠቁመው

አመራሩ ህዝብ የሚያነሳቸውን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ አሁንም በቁርጠኝነት አጠናክሮ ሊሰራ ይገባልም ብለዋል።

በከተማው የተጀመረው የኮሪደር ልማት ስራ በጥሩ ደረጃ ላይ ያለ ሲሆን በተለይ የሀብት አሰባሰብ ስራው በትኩረት መሰራት እንዳለበት ገልጸዋል ።

ባለፉት ዘጠኝ ወራት አቅደን ያልተሳኩ ተግባራት በቀሪ ወራቶች ውስጥ በመፈፀም የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ መስራት ይኖርብናል ሲሉ አቶ ታደለ አሳስበዋል።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የጤና ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሙባሪክ ዘይኑ በበኩላቸው በከተማ ግብርናው ዘርፍ ተስፋ ሰጪ ተግባራት ቢኖሩም ከሌሎች ቦታዎች ተሞክሮዎችን በመቀመር አጥጋቢ ውጤቶችን ልናስመዘግብ ይገባል ብለዋል።

አቶ ሙባሪክ አያይዘውም አሰራሩን ጠብቆ የሚሄድ የንግዱ ማህበረሰብ መፍጠር እንደሚገባ ጠቁመው ከስራ ዕድል ፈጠራና ያልተመለሱ ውዝፍ ዕዳዎችን ከማስመለስ አንፃር ትኩረት መስጠት እንደሚያስፈልግም አንስተዋል።

እንደ ፓርቲ ጽህፈት ቤት ባለፉት ዘጠኝ ወራት ያልተሳኩ ተግባራትን በቀጣይ 9O ቀናት ላይ የዕቅድ አካል አድርጎ ለመስራት በሚያስችል መልኩ ሰነድ ቀርቦ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል።

Previous ከንቲባ ችሎት በህብረተሰቡ ዘንድ የሚነሱ የልማትና መልካም አስተደደር ጥያቄዎችን እና ቅሬታዎችን አግባብነት ባለው መልኩ መልስ ለመስጠት ያለው ጠቀሜታ ከፍተኛ ነው።

Leave Your Comment

የቋንቋ አማራጭ

🇺🇸 English
🇪🇹 አማርኛ
🇪🇹 Afan Oromo