ሚያዝያ O1/2O17 ዓ/ም [ወልቂጤ]
በጉራጌ ዞን የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር የካቢኔ አባላት የባለፉት ዘጠኝ ወራት የስራ አፈፃፀሞችን በመገምገም አቅጣጫዎችን አስቀመጠ።
በከተማው ለሚከናወነው የኮሪደር ልማት ስራ ህብረተሰቡ የማሳተፉ ስራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ተገልጿል።

የካቢኔ አባላቱ በከተማ አስተዳደሩ ባለፉት ዘጠኝ ወራት የተከናወኑ ስራዎችን በጥልቀት የገመገሙ ሲሆን በዚህም ባለፉት ዘጠኝ ወራት በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊና በፖለቲካው ዘርፍ አመርቂ ተግባራት መከናወናቸውንና በድክመት የተለዩ ጉዳዮች ደግሞ በቀጣይ እንዲታረሙ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል።
በከተማው የተጀመረው የኮሪደር ልማት ስራ በጥሩ ደረጃ ላይ ያለ ሲሆን በተለይ ከወሰን ማስከበር ጋር የተያያዙ ጉዳዮች በትኩረት መሰራት እንዳለበት ተገልጿል።

ልማትን ለመስራት ገቢን በአግባቡ መሰብሰብ ወሳኝ መሆኑን በጥልቀት የገመገሙት የካቢኔ አባላቱ ገቢን በአግባቡ መሰብሰብ ወሳኝ መሆኑንና ህገ-ወጥ ነጋዴዎችን ህጋዊ ማድረግ እንደሚገባም ተወያይተዋል።
በፀጥታው ረገድ ማህበረሰቡን ያሳተፈ ስራ እየተሰራ በመሆኑ በሰላሙ ዙሪያ የተሻለ መሆኑ ተገልጿል።

በጤናው ረገድም በጤና ተቋማት የሚሰጡ አገልግሎቶችን ቀልጣፋ የማድረግና በቂ መድኃኒት እንዲኖር መደረግ እንዳለበትም በውይይቱ ተነስቷል።
በትራንስፖርት ዘርፍም ህገ-ወጥ ተግባራትን የመከላከሉ ስራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትና በተለይ ዕድሜያቸው ያልደረሱ ህፃናት መንጃ ፍቃድ ሳይዙ ባጃጅ የሚይዙበት ሁኔታ መኖር እንደሌለበት የካቢኔ አባላቱ አንስተዋል።
በከተማው የሚሰሩ የልማት ስራዎች ላይ በአንዳንድ አካባቢዎች የጥራት ጉድለት መስተዋሉ፣ የእሳት አደጋ መኪና ሰራተኞች ካምፕ በማዘጋጀት በፈረቃ እንዲሰሩ ማድግ እንደሚገባም ተመላክቷል።
በትምህርትና ስራ ዕድል ፈጠራ፣ በሴቶችና ህፃናት፣ በወጣቶች እና በከተማ ግብርና መስክ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ተጠቁሟል።

በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ሙራድ ከድር እንደገለፁት ባለፉት ዘጠኝ ወራት በርካታ የልማት ስራዎች ማሳካት መቻሉን ጠቁመው አመራሩ ህዝብ የሚያነሳቸውን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ አሁንም በቁርጠኝነት ሊሰራ ይገባል።
ባለፉት ዘጠኝ ወራት አቅደን ያልተሳኩ ተግባራት በቀሪ ወራቶች ውስጥ በመፈፀም የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ መስራት ይኖርብናል ሲሉ ክቡር ከንቲባው ተናግረዋል።
በተለይ አመራሩ ሌብነትን መጠየፍ አለበት ያሉት ክቡር ከንቲባው በከተማው የተጀመሩ የካፒታል ፕሮጀክቶችን በጊዜና በጥራት ለማጠናቀቅ እርብርብ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።

ከስራ ዕድል ፈጠራና ያልተመለሱ ውዝፍ ዕዳዎችን ከማስመለስ አንፃር ትኩረት መስጠት እንደሚያስፈልግም አንስተዋል።
ከተማዋ ከዕዳ የፀዳች በማድረግ በቀጣይ ለወጣቶች በቂ የስራ ዕድል ለመፍጠር በትኩረት እየተሰራ መሆኑንና ጠቁመዋል።
በትራንስፖርት ዘርፍ፣ በንግድና በሌሎች መስኮችም የሚስተዋሉ ህገ-ወጥነትን ለመከላከል በቅንጅት እንደሚሰራም ተናግረዋል።
እንደ ከተማ አስተዳደሩ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ያልተሳኩ ተግባራትን በቀጣይ 9O ቀናት ላይ የዕቅድ አካል አድርጎ ለመስራት በሚያስችል መልኩ ሰነድ ቀርቦ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል።

