የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያዊ ክልል የጉራጌ ዞን ዋና ከተማ በወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ቀደም ሲል ተፈራ ሆቴል ተብሎ ይጠራ የነበረው በከተማው መሀል ላይ የሚገኝ 5333.05 (አምስት ሺ ሶስት መቶ ሰላሳ ሶስት ) ካሬ ሜትር ስፋት ያለው ቦታ የወልቂጤ ከተማ ማዘጋጃዊ ቤታዊ አገልግሎት ደረጃውን ለጠበቀ ሞል ወይም ሆቴል ግንባታ እንዲውል ለዓልሚዎች በልዩ ጨረታ ማስተላለፍ ይፈልጋል ።

በዚህም መሰረት ከመጋቢት 10/2017 ዓመተ ምህረት ጀምሮ ለሀያ (20) ተከታታይ የስራ ቀናት በወልቂጤ ከተማ አስተዳደር መዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ቅጥር ግቢ ውስጥ የጨረታ ሰነድ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

#የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በወጣው አዋጅ 721/2004 መሰረት የተዘጋጀ የጨረታ ሰነድ እንደ ሚከተለው ቀርቧል:-
ክፍል አንድ፡ የጨረታ መመሪያ
1. ማንኛዉም ተጫራች ከዚህ በታች የተቀመጠዉን የጨረታ መመሪያ መሰረት መፈጸም ይኖርበታል፡፡ ከመመሪያው ውጭ የቀረቡ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
1.1.1 ኦሪጂናል እና የመ/ቤቱ ማህተም ያረፈበት ሰነድ ብቻ ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡ የመ/ቤቱ ክብ ማህተም ያላረፈበት ኦሪጂናል ያልሆነ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለዉም፡፡
1.1.2 በአንድ የጨረታ ዙር ለተመሳሳይ የመሬት አገልግሎት ከአንድ ቦታ በላይ የጨረታ ሰነድ መግዛትና መወዳደር አይችልም፡፡
1.1.3 ተጫራቾች በጨረታ ዋጋ ማስገቢያ እና የሀሳብ ማቅረቢያ ላይ የተመለከቱትን በጥንቃቄ እና በግልጽ ሊነበብ በሚችል መልኩ ማስፈር ይኖርበታል፡፡
1.1.4 በግልጽ የማይነበቡ ስርዝ ድልዝ የበዛባቸው ሰነዶች ከጨረታዉ ዉጪ ይደረጋሉ፡፡
1.1.5 በዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ የሚጫረትበትን የቦታ ዋጋ በፊደል እና በአሃዝ መሞላት አለበት፡፡በፊደል እና በአሀዝ በተፃፈዉ መካከል ልዩነት ካለ በፊደል የተፃፈዉ ተቀባይነት አለው፡፡
1.1.6 ሌላ ተጫራች በሰጠዉ ዋጋ በመንተራስ ዋጋ መስጠት አይቻልም፡፡
1.1.7 በጨረታዉ የሚሳተፈዉ አካል /ድርጅት ወይም ማህበር/ ከሆነ ህጋዊ የሆነ የድርጅቱ ማህተም በሰነዶቹ ሁሉም ገፅ ላይ ማኖር ይኖርበታል፡፡
1.1.8 ተጫራች የዋጋ እና የሀሳብ ማቅረቢያ ሰነዶቹን በአግባቡ በመሙላት እና በታሸገ ኤንቨሎፕ ላይ የተጫራች ስም እና የቦታዉ ልዩ ፕሎትና የፕሎት ቁጥር በግልጽ በመጻፍ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ በተቀመጠዉ የጊዜ ገደብ ዉሰጥ ማሰገባት ይኖረባቸዋል፡፡ የጨረታ ሳጥን ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ ማንኛዉም ሰነድ ዋጋ አይኖረዉም፡፡
1.1.9 ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ የተጫረተበትን ቦታ ስፋት በቦታዉ የመነሻ ዋጋ በማባዛት የሚገኘዉን ዉጤት(20) ከሃያ በመቶ ያላነሰ በማዘጋጃ ቤቱ ስም በማስገባት ከዋጋ እና የሀሳብ ማቅረቢያ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
1.1.10 የሚቀርበው የቅድመ ክፍያ መጠን ከአጠቃላይ የጨረታ ዋጋ ለንግድ ከ25 በመቶ ማነሰ የለበትም፡፡
1.1.11 ማ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰርዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
1.2 ከጨረታ ዉጪ የሚያስደርጉ ድርጊቶች
1.2.1 የተጭበረበረ ወይም ከሚፈለገዉ በታች የጨረታ ማስከበሪያ ሰነድ ያቀረበ ተጫራች፣
1.2.2 የተጭበረበረ የህጋዊ ሰዉነት ማረጋገጫ እና የዉክልና ማስረጃ ሰነድ ያቀረበ ተጫራች፣
1.2.3 በአዋጁ መሰረት በከተማዉ በወጡ ጨረታዎች አሸንፎ ዉል ሣይፈጽም ቀርቶ ገደብና ቅጣት የተጣለበት የጊዜ ገደብ ያልተጠናቀቀ ተጫራች ከሆነ፤
1.2.4 በሌሎች ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ያስገባ ወይም በጨረታ ዋጋ ላይ ከሌሎች ተጫራቾች ጋር የተመሳጠረ ከሆነ
1.2.5 ተጫራቹ ቀደም ሲል በወሰደዉ መሬት ላይ ከ50% በታች ሳያጠናቅቅ ሁለት ጊዜ የመሬት የመጠቀም መብቱን ያሰተላለፈ መሆኑንና ግንባታ ባለማጠናቀቁ መሬት ተነጥቆ የተወሰነበት የቅጣት ዘመን ያልተጠናቀቀ ከሆነ፣
1.2.6 የጨረታዉን ሂደት የሚጻረሩ ወይም የሚያዛቡ ድርጊቶች የተፈጸመ ሲሆን፡፡
1.3 የጨረታ ማወዳደሪያ መስፈርት እና ሌሎች ማብራሪያዎች
1.3.1 ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የሊዝ ጨረታ ዋጋ ከመቶ ሰማንያ (80%) ነጥብ ሲኖረው፣የቅድመ ክፍያ መጠን ከመቶ አስራ ሁለት (12%) እና ክፍያ ማጠናቀቂያ ጊዜ ከመቶ ስምንት (8%) ይኖረዋል፡፡
የጨረታ አሸናፊ የሚለየው በሦስቱ ነጥቦች ድምር በሚገኘው ውጤት ነው፡፡
1.3.2 ሁለት እና ከዚያ በላይ ተጫራቾች በሶስቱም መወዳደርያ መስፈርቶች እኩል ያመጡ ከሆነ ባቀረቡት የህንፃ ከፍታ የሚለዩ ሲሆን በሁሉም መስፈርቶች እኩል ከሆኑ ግን አሸናፊዉ በእጣ ይለያል፡፡ በሁሉም መስፈርቶች እኩል ወጥተዉ ሴት ብቸኛ ተወዳዳሪ ካለች ቅድሚያ ይሰጣታል፡፡
1.3.3 አሸናፊ ተጫራች ማሸነፉ እንደተገለጸለት በአስር የስራ ቀናት ጊዜ ዉስጥ በጨረታ ሰነድ ላይ የተገለፀውን ቅድመ ክፍያ በመክፈል የሊዝ ዉል ይፈጽማል፡፡ በተጠቀሰዉ ቀን እና በተጨማሪ በማስጠንቀቂያ በሚሰጠዉ ጊዜ ያልቀረበ ተጫራች ከጨረታዉ ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ እንዲሆን ይደረጋል፡፡ ሁለተኛ እና ሶስተኛ የወጡት ጫራቾች አንደኛ በወጣዉ ዋጋ ለመዉሰድ ከፈለጉ እንደየቅደም ተከተላቸው ይሰጣቸዋል፡፡ ጨረታዉ ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የጨረታ ዋጋ እና ሀሳብ ላይ ማሻሻያ ማድረግ እና ከጨረታዉ ራሳቸዉን ማግለል አይችሉም፡፡
1.3.4 የጨረታ ሰነድ መሸጫ ቀን ከ10/07/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለ20 ተከታታይ የስራ ቀናቶች ሲሆን በ8/08/2017 ዓ.ም እስከ ቀኑ 6፡00 (ስድስት ሰዓት) የጨረታ ሰነድ የሚሸጥ ሲሆን ከ ቀኑ 9፡30 አስከ11፡00 (አስራአንድ ሰዓት) የጨረታ ማስገቢያ ጊዜ ሆኖ የጨረታ ሳጥን የሚታሸገው በዛው ዕለት ከቀኑ11፡30 አስራ አንድ ሰዓት ተኩል) ሲሆን ጨረታው በማግስቱ 09/08/2017 ዓ.ም ተጨራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 3:00 (ሶስት ሰዓት) በወ/ከ ከንቲባ አዳራሽ አዳራሽ የሚከፈት ይሆናል፡፡
1.3.5 ተጫራቾች ቦታው በአካል መመልከት ከፈለጉ ከጨረታ አስፈፃሚ ቡድን ጋር በመሆን 18/07/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 መጎብኝት ይችላሉ፡፡ ከዚህ ውጪ ባለው ጊዜ በፕላን መመልከት ይቻላል፡፡




