የካቲት 17/2O17 ዓ/ም [ወልቂጤ]
የብልጽግና ፓርቲ የሀገርን ብልጽግና ለማረጋገጥ እየሰራ መሆኑን የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ አባልና የኢፌድሪ ከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ሚንስትር ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ ተናገሩ።

የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባዔ ውሳኔዎችና ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ከወልቂጤ ከተማ ህዝብ ጋር ውይይት ተደርጓል።
የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ አባልና የኢፌድሪ ከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ሚንስትር ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ በብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባዔ የተቀመጡ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎችን ለህዝቡ አቅርበው ውይይት ተደርጓል።
ሚንስትሯ እንዳሉት ብልጽግና ፓርቲ የህዝቦችን የልማት ጥያቄ ለመፍታት እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

በፓርቲው የተገኙ ስኬቶች የብልጽግና ጉዞን ለማረጋገጥና ሀገራዊ ዕድገትን ለማፋጠን እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
በሀገራዊ ለውጡ የተመዘገቡ ስኬቶችን ማስቀጠል የብልጽግና ፖርቲ የመጀመሪያው አጀንዳ መሆኑንም ገልፀዋል።
ፓርቲው እንደ ሀገር ከ15 ሚሊዮን በላይ አባላት ያሉት መሆኑን ጠቅሰው ብቃትና ጥራት ያለው አመራር ለማፍራት በትኩረት እየተሰራ እንደሆነም ጠቁመዋል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታሁን አብዲሳ እንዳሉት የጉራጌ ህዝብ የስራ ባህል ለሌሎች አካባቢዎች በአብነት የሚጠቀስ እንደሆነ ተናግረዋል።
ህዝቡ ለብልጽግና ፓርቲ ያለውን ድጋፍ ያሳየበት ሁኔታ የፓርቲውን አላማ በግልጽ መረዳቱን ያሳያል ሲሉም ገልጸዋል።
በህዝቦች መካከል ጠብ ለመጫር የተሞከሩ ስራዎች የክልሉ መንግስት ማክሸፍ መቻሉን ተጠቁመዋል።

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ ባለፉት ሶስት አመታት በተሰሩ የልማት ስራዎች በሁሉም ዘርፍ አበረታች ለውጦች መመዝገቡን ተናግረዋል።
በቀጣይም የተስተዋሉ ውስንነቶችን በመፈተሽ የተሻለ ለውጥ ለማምጣት እንደሚሰራ ተናግረዋል።
በልማቱ የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥሉ አመላክተዋል።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ሙራድ ከድር አስተዳደሩ ነዋሪውን በማሳተፍ የሚያከናውናቸው የልማት ራዎችች ውጤት የተመዘገበበት መሆኑን ተናግረዋል።
በማህበራዊ ጉዳይ ህዝብን በማሳተፍ ለአቅመ ደካሞች የመኖሪያ ቤቶች የመስራትና የማድስ ሥራ በማከናወን በርካቶችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉንም ክቡር ከንቲባው ተናግረዋል።
የከተማው የንፁህ መጠጥ ውሃ በዘላቂነት ለመፍታት የተጀመሩ ስራዎች አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።

በኢኮኖሚ ዘርፍም ኢንቨስትመንትን በማስፋፋት ዜጎች በስራ ዕድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ መደረጉን አመላክተዋል።
ህዝባዊ መድረኩ እነዚህን ተግባራት የበለጠ ለማጠናከርና የጋራ አረዳድን ለማምጣት አጋዥ መሆኑንም ተናግረዋል።
አንዳንድ የመድረኩ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት የውይይት መድረኩ አስተያየታቸውን በግልፅ እንዲናገሩ እድል የፈጠረ መሆኑን ተናግረዋል።

በቀጣይ ሊከናወኑ በሚገባቸው የልማትና የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ዙሪያ በከተማው በሚከናወኑ ሁለንተናዊ የልማት ተግባራት ተባባሪ ለመሆን ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል።
በህዝባዊ የውይይት መድረኩ የህብረተሰቡ ተወካዮች፣ የባህልና እምነት አባቶች፣ የክልል፣ የዞንና የከተማው የስራ ሃላፊዎች ታድመዋል።

