የጉራጌ ማህበረሰብ የሴቶችን መብት አስቀድሞ የተረዳና ለሴቶች የእኩልነት ትግል ያረጋገጠ መሆኑ አንትሮሽት አንዱ ማሳያ መሆኑ የጉራጌ ዞን አስተዳደር አስታወቀ።

ጥር 17/2017 ዓ.ም

የጉራጌ ማህበረሰብ የሴቶችን መብት አስቀድሞ የተረዳና ለሴቶች የእኩልነት ትግል ያረጋገጠ መሆኑ አንትሮሽት አንዱ ማሳያ መሆኑ የጉራጌ ዞን አስተዳደር አስታወቀ።

በጉራጌ ዞን የእናቶች ቀን (አንትሮሽት) በእዣ ወረዳ ያስሁራና የዋርበያ ቀበሌ በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት ተከበረ።

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ እንዳሉት የጉራጌ ማህበረሰብ ከኢትዮጵያ ህገ መንግስት ድንጋጌ አስቀድሞ የጾታ እኩልነት ያረጋገጠ ህዝብ ነው።

ከእነዚህም አንዱ አንትሮሽት አንዱ ሲሆን ለወጣት ሴቶች ልጃገረዶች ነቐ ፣የገንየ ፣ ለወጣት ወንዶች ለበሞ ፣ላገቡ ሴቶች ይፍትዝፓር እንዲደረግልላቸው አስቦና ተረድቶ የተገበረ ማህበረሰብ መሆኑን አስታውቀዋል።

ይህ የመሰለ በዓል ተቀዛቅዞ የነበረ ቢሆንም የዞኑ መንግስት በሰጠው ልዩ ትኩረት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን በየአመቱ በፌስቲቫል ደረጃ እንዲከበር ተደርጓል ነው ያሉት።

ዋና አላማውም ባህላችን በመጤ ባህሎች በመከላከል በሀገር አቀፍ ደረጃ በሞዴልን ተወስዶ የኢትዮጵያ የእናቶች ቀን ሆኖ እንዲከበር እና ወደፊትም በአለም አቀፍ ቅርስነት ተመዝግቦ የቱሪዝም ሀብት እንዲሆን ለማስቻል ነው ሲሉ አቶ ላጫ አስገንዝበዋል።

አክለውም በዓሉ በብሄረሰቡ ዘንድ ያሉትን የመከባበርና የሰላም እሴቶቻችንን ይበልጥ እንዲለሙ የሚደረጉበት፣ ሴቶች መብታቸው እንዲያስከብሩና ተጠቃሚነታቸውን እንዲያረጋግጡ ትልቅ ፋይዳ አለው ብለዋል።

የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሴቶችና ህጻናት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ዘቢባ መሀመድ እንዳሉት የጉራጌ ማህበረሰብ የሴቶችን መብት በማክበር ዘመኑን የቀደመ ለሴቶች የእኩልነት ትግል ያረጋገጠ መሆኑ አንትሮሽት ማሳያ እንደሆነ ገልፀዋል።

አያይዘውም የቃቄ ወርድወትም ስለ ሴቶች መብት በማይነገርበት ወቅት ስለሴቶች እኩልነት የታገለች ናት ያሉት ወ/ሮ ዘቢባ ይህ ደግሞ ለሴቶች ክብርና ነጻነት ከጥንት ጀምሮ የታገለ ማህበረሰብ መሆኑን ተጨማሪ ማስረጃ መሆኑ ተናግሯል።

የጉራጌ ዞን ሴቶችና ህጻናት መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ነጅሚያ መሀመድ በበኩላቸው አንትሮሸት የጉራጌ ብሔረሰብ ከጥንት ዘመን ጀምሮ የሴቶችን ክብር የሚዘክርበት ድንቅ ባህሉ ነው።

በሌላ አጠራር አሁን በዘመናዊ መልኩ በየ ዓመቱ በፈረንጆቹ ማርች 8 የሴቶች ቀን ብለን የምናከብረውን በዓል ማለት እንደሆነ አብራርተዋል።

የእናቶች ኃላፊነት የተረዳው የጉራጌ ማህበረሰብ የእናቶች ክብር ለመግለጽ ሲል የአንትሮሽት በዓል መፍጠር የቻለና የአርቆ አሳቢነት ምልክት ነው ሲሉ ኃላፊዋ ገልጸዋል።

አንትሮሽት ልጆች ለእናታቸው፤ እንዲሁም ባል ለሚስቱ ያላቸውን ፍቅርና አክብሮት የሚገልፁበት፤ ምስጋናቸውን የሚያቀርቡበት፣ስለራሳቸው የሚወያዩበትና በዓል ነው ያሉት ወ/ሮ ነጅሚያ በዓሉ በሀገር እና በዓለም አቀፍ ደረጃ የበለጠ እንዲተዋወቅ የሚመለከተው ሁሉ አስተዋጾኦ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።

የእዣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘዉዱ ዱላ አንትሮሽት ለሴቶች ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ተጠቃሚነትታቸው ያረጋገጠ በዓል እንደሆነ ተናግረዋል።

በእለቱ ያገኘናቸው እናቶች እንዳሉት አንትሮሸት፣የደስታ ፣የሰላም ፣የእኩልነት ፣የነጻነት ቀናችን በመሆኑ በልዩ ልዩ ድምቀቶች እያከበርነው እንገኛለን።

በእለቱም ዝማሙጃት ፣የጎመን ክትፎ ፣ቆጮ ፣ ጥሬ ስጋ፣ክትፎ ፣አይብ ፣ጠላ እና ሌሎች በርካታ የምግብ አይነቶች ተዘጋጅተው ቤተሰብ ሁሉ በጥጋብ እንዲያሳልፍ ይሆናል።በእለቱም በምግብና በመጠጥ፣በጭፈራ እና በመከባበር እንዲሁም በእረፍት እንደሚያከብሩት ተናግረው ይህ በዓል ተቀዛቅዞ ከነበረበት አሁን ደምቆ እየተከበረ በመሆኑ ለሴቶች ደግሞ የሚያሰገኘው ጠቅም ከፍተኛ እንደሆነ አስገንዝበዋል።

በእለቱም በዓሉን የሚገልጹ ኪነ ጥበባዊ ስራዎች ለታዳሚው የቀረቡ ሲሆን በዞኑ ላሉ ሞዴል የልማት ህብረት መሪ ሴቶች ፣አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት እውቅናና ሽልማትም ተደርጎላቸዋል

Previous የኮሪደር ልማት ስራ ከዚህ በፊት የነበረውን የመልማት ቁጭት የሚቀርፍና ለቀጣይ ትውልድ የምናስተላልፈው አሻራችን በመሆኑ የወጣቱ ንቁ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ።

Leave Your Comment

የቋንቋ አማራጭ

🇺🇸 English
🇪🇹 አማርኛ
🇪🇹 Afan Oromo