ጥር 17/2017

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከወጣቶች ጋር “የድርሻዬን እወጣለሁ ለከተማዬ አሻራዬን አኖራለሁ::” በሚል መሪ- ቃል የወልቂጤ ከተማ የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ምክትል አስኪያጅ በአቶ ጸጋ ፍቅሬ ሰነድ ቀርቦ ሰፊ የሆነ የምክክር ተካሂዷል።
የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ የሆኑት አቶ ሙራድ ከድር እንዳሉት የኮሪደር ልማቱን ለማሳካት የወጣቱ ሚና ከፍተኛና ለትውልድ የምናስተላልፈው አሻራችን በመሆኑ የወጣቱ ንቁ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑ ጠቁመው።

የኮሪደር ልማቱ በከተማችን መሠራቱ የከተማውን ገጽታ ከመቀየር ባሻገር የገቢ አቅምን ከማሳደግ አንጻር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረውም ተናግረዋል።
ወጣቱ በዚህ ልክ ቀድሞ ተወያይቶ ለኮሪደር ልማቱ ቃል የገባበት ሁኔታ በጣም የሚያስደስትና ለተሻለ ሥራ የሚያነሳሳ መሆኑንም ገልፀወ።
በየደረጃው ካሉ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት ተደርጓል ቀጣይም ማህበረሰቡን በነቂስ በማሳተፍ ወጣቱ ከትች፣ ከሃሜት በመውጣት በመደማመጥና በመደጋገፍወደ ተግባር መግበት እንዳለበት አቶ ሙራድ ከድር ገልጸዋል።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ የሆኑት አቶ ጴጥሮስ አስራት በበኩላቸው በርካታ መድረኮችን ከማህበረሰቡ ጋር መደረጉን ጠቁመው ኮሪደር ልማት ለከተማችን ወሳኝ ነው የተገኘውን እድል መጠቀም ካልቻልን ታሪክ ይወቅሰናል ስለዚህ በዕድሉ ልንጠቀምበት ይገባል ካሉ በኋላ
ወጣቱ ዛሬ ባሳየው ቁርጠኝነትና ተነሳሽነት በማጠናከር ከመቼውም ጊዜ በተሻለ መልኩ በመተጋገዝ ከመንደርተኝነት ሃሳብ በመላቀቅ በእኔነት መንፈስ በአንድ ድምፅ ለከተማችን ልማት በመተባበር መስራት ያስፈልጋል ሲሉ ገልጸዋል።
አቶ ጴጥሮስ አክለውም ተግባሩን ለማሳካት በምንሰራበት ወቅት የሚገጥሙትን መሰናክሎች በብልሃትና በማስተዋል በማለፍ የታለመውን ልማት ተግባራዊ ለማድረግ እየተሰራ እንደሚገኝ አብራርተዋል።

አንዳንድ በዉይይቱ ወቅት የተገኙ ወጣቶች እንደገለፁት ይህ ልማት ከዚህ በፊት የነበረብንን የልማት ቁጭት በእጅጉ የሚመልስልን በመሆኑ እንደ ወጣት በሚፈለገው መልኩ ከልማቱ ጎን እንሆናለን ያሉ ሲሆን
ከተማችን አለማችም ከሚል ቁጭት በመውጣት ለማልማት በቁርጠኝነት እንሰራለን በልማት ጉዳይ ወጣቱ ምንም ድርድር የለውም በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ብዙ ተከታይ ያለው ወጣት በሚዲያው የማስተባበር ሥራ ሊሠራ ይገባል ሲሉ ገልጸው።
ከሰፈር ከመከፋፈል ሃሳብ ወጥተን እርስ በእርስ በመተሳሰብ በአንድነት ተጋግዘን ለከተማችን ልማት ከቆምን በዚህ ዓመት ብቻ ከፍተኛ ለውጥ ይመጣል ሲሉ ወጣቶቹ ተስፋቸውን አመላክተዋል።

ከኮሪደር ልማቱ ጎን ለጎን ከተማው ላይ ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ህንፃዎች እንዲጠናቀቅ ማድረግ ያረጁ ቆርቆዎች በማንሳት የተሻለች ውብና ሳቢ ከተማ እንድትሆን ተጋግዘን ልንሰራበት ይገባል ሲሉ ወጣቶቹ አንስተዋል።
በመጨረሻም በከተማችን በየትኛውም በኩል በሚደረጉ የልማት እንቅስቃሴዎች ላይ ከከተማው አስተዳደር ጎን እንደሚሆኑና ሊሰራ የታሰበውን የኮሪደር ልማትን ለመደገፍ 588,500 ብር ድጋፍ ለማድረግ ወጣቶቹ ቃል ገብተዋል።
ዘገባው የከተማ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ነው።

