
ጥር 16/201017(ወልቂጤ)
“በከተማዬ የኮሪደር ልማት ስራ ላይ ሁለንተናዊ ተሳትፎ አደርጋለሁ”።
የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር “በከተማዬ የኮሪደር ልማት ስራ ላይ ሁለንተናዊ ተሳትፎ አደርጋለሁ” በሚል መሪ ቃል በአቶ ይብጌታ ንጋ የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ስራ አስኪያጅ ሰነድ ቀርቦ በከተማ አስተዳደሩ ከሚገኙ የነጋዴ ማህበረሰቦች ውይይት አካሄዱ።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ የሆኑት አቶ ሙራድ ከድር በበኩላቸው ከተማችን ወልቂጤ የብዙ ታሪክ ባለቤት ብትሆንም ካላት ዕድሜ አንጻር ያለመልማቷን በቁጭት አንስተው ዛሬም ወልቂጤን ለማልማት በቁርጠኝነት ከተነሳን የማናሳካበት ምክንያት ስለሌለ ተረባርበን ይህንን ልማት ልናፋጥን ይገባል ብለዋል።

አያይዘውም የኮሪደር ልማት ፕሮጀክቱን ዳር እንዲደርስ ለማድረግ በከተማችን የሚገኘው የነጋዴው ማህበረሰብ ክፍል ከፍተኛውን ድርሻ የሚወስድ ሲሆን በየደረጃው የድርሻውን እንዲወጣ መልዕክት አስተላልፈዋል
የኮሪደር ልማቱ በከተማችን መሠራቱ የከተማውን ገጽታ ከመቀየር ባሻገር የገቢ አቅምን ከማሳደግ አንጻር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተናግረዋል።

ስለሆነም በከተማው የሚኖር ነዋሪ የሆነ ማህበረሰብ ሁሉ በዚህ የኮሪደር ልማትና በሌሎች የልማት ፕሮጀክት ላይ ተሳታፊ እንዲሆን አሳስበዋል።
የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ታደለ በቀለ በመድረኩ እንደተናገሩት የኮሪደር ልማት ስራ የብልጽግና ፓርቲ ኤኒሼቲቭ እንደመሆኑ፤ ከተማን ለኑሮ ሳቢና ምቹ ከማድረግም ባለፈ የስራ ዕድል ከመፍጠረ አንጻርም ትልቅ ድርሻ እንዳለው ተናግረዋል።
አቶ ታደለ አክለውም ነጋዴው ማህበረሰባች በዚህ የኮሪደር ልማት ብቻም ሳይሆን በሌሎች የልማት ስራዎች ላይ የማያቋርጥ ዕገዛም ማድረግ እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

በዉይይቱ የተገኙት የነጋዴ ማህበረሰቦች ለከተማችን የኮረደር ልማት መሳካት ገንዘባችንን ብቻ ሳይሆን እስከ ህይወት መስዋዕትነት ከልማቱ ጎን እንደሚቆሙ ገልጸዋል።
ተሳታፊዎቹ አያይዘውም ይህ ልማት ከዚህ በፊት የነበረብንን የልማት ቁጭት በእጅጉ የሚመልስልን በመሆኑ በምናደርገው ድጋፍ ደስተኞች ነን ሲሉ አንስተዋል።

አክለውም ይህንን የኮሪደር ልማት ለማሳካት የተጀማመሩ የገቢ አሰባሰብ እንቅስቃሴዎች መጠናከር እንዳለበትና ለተግባሩ መሳካ ከገንዘብ መዋጮ ባሻገር በማስተባበሩም ላይ ንቁ ተሳታፊ እንደሚሆኑም ተሳታፊዎች አንስተዋል።
በከተማችን በየትኛውም በኩል በሚደረጉ የልማት እንቅስቃሴዎች ላይ ከከተማው አስተዳደር ጎን እንደሚሆኑና የሚጠበቅባቸውን የገንዘብ መዋጮ ተሳታፊ እንደሚሆኑ ቃል በመግባት መድረኩ ተጠናቋል





