በወልቂጤ ከተማ አስተዳደር የሚገኙ አጠቃላይ የመንግስት ሰራተኞች እና አመራሮች “ለከተማዬ የኮሪደር ልማት ስራ ላይ ተሳትፎ አደርጋለሁ” በሚል መሪ ቃል ውይይት አደረጉ።

ጥር 14/2O17 ዓ/ም [ወልቂጤ]

“በከተማዬ የኮሪደር ልማት ስራ ላይ ሁለንተናዊ ተሳትፎ አደርጋለሁ”።

በወልቂጤ ከተማ አስተዳደር የሚገኙ አጠቃላይ የመንግስት ሰራተኞች እና አመራሮች “ለከተማዬ የኮሪደር ልማት ስራ ላይ ተሳትፎ አደርጋለሁ” በሚል መሪ ቃል ውይይት አደረጉ።

የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ከመስጠቱም ባሻገር ዜጎች ጽዱና ምቹ አካባቢዎች ለይ ኑሯቸውን እንዲመሩ በማደረግና የከተማ ገጽታንም በመቀየሩ ረገድ ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል።

የኮሪደር ልማት በከተማችን መሠራቱ የቱሪስት ፍሰት በመጨመር ኢኮኖሚን ከማሳደግ ባለፈ የሀገራችንን ትልቅ ችግር የሆነውን ስራ አጥነት በመቀነስ ለዜጎች የስራ ዕድል እንደሚፈጥር ተገልጿል።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደርም ለዚህ የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት መሳካት በከፍተኛ ሁኔታ እየተንቀሳቀሰ ሲሆን ሀብት ለማሰባሰብ ከከተማው ማህበረሰብ ጋር ለመወያየት ዝግጅት ማጠናቀቁም ተገልጿል።

በከተማው ከመንግሥት ሠራተኞች ጋር በጉዳዩ ዙሪያ ውይይት የተደረገ ሲሆን ቀደም ብሎ በአመራር ደረጃ በተደረገዉ ዉይይትም አመራሩ ድጋፍ ለማድረግ መስማማታቸው ተገልጿል ።

በውይይቱ የተሳተፉ የመንግስት ሠራተኞች በከተማው ሊሰራ በታቀደው የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ስራ መደሰታቸውንና ከደመወዛቸው በሻገር በጉልበት ጭምር ለማገዝ ዝግጁ መሆናቸውም ጠቁመዋል።

አያይዘውም ለኮሪደር ልማቱ የተጀመረው የገቢ አሰባሰብ ስራ ተጠናክሮ መሄድ እንዳለበት ገልጸዋል።

የኮሪደር ልማት ስራ ከዚህ በፊት የነበረብንን የልማት ቁጭት የሚቀርፍና ለቀጣይ ትውልድ የምናስተላልፈው ቅርስ በመሆኑ አመራሩና ባለሙያው በመቀናጀት የድርሻቸውን ሊወጡ ይገባል ሲሉም አንስተዋል።

የውይይት መድረኩን የመሩት አመራሮች በበኩላቸው የመንግስት ሰራተኛው ለኮሪደር ልማት ስራው እንቅስቃሴ እውን መሆን ላሳየው ተነሳሽነት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በቀጣይም በከተማ አስተዳደሩ በሚደረጉ የልማት ስራዎች ላይም ሌሎችም ባለድርሻ አካላትም የድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባም መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

ይፋ የተደረገውን የ25 ኪሎ ሜትር የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ስራ የከተማ አስተዳደሩ የመንግስት ሰራተኞችና አመራሮች ከደመወዛቸው በመጀመሪያ ዙር ተቆራጭ የሚሆን ከ2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ለመስጠት ቃል ተገብተዋል።

Previous ጤና ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ ስርዓታቸውን በማስፋት ጤናማ ዜጋና ማህበረሰብ ለመፍጠር እያደረጉት ያለው ተግባራት ማስቀጠል መቻል እንዳለባቸው የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ጤና ፅህፈት ቤት አስታወቀ ።

Leave Your Comment

የቋንቋ አማራጭ

🇺🇸 English
🇪🇹 አማርኛ
🇪🇹 Afan Oromo