የባህል ሽማግሌዎች የየአካባቢዉን ባህላዊ እሴቶችና የእርቅ ሥርዓቶች መሠረት አድርገዉ ችግሮችን መፍታት ይጠበቅባቸዋል ፦ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ ዶ/ር

የየአካባቢዉ የባህል ሽማግሌዎች የየአካባቢዉን ባህላዊ እሴቶችና የግጭት መፍቻ ሥርዓቶችን መሠረት አድርገዉ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችንና አለመግባባቶችን መፍታት እንደሚጠበቅባቸውም ርዕሰ መስተዳድሩ አሳስበዋል ።መረጃው የክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ነው

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር እንዳሻዉ ጣሰው፣ ከስልጤ ብሔረሰብ የባህል ሽማግሌዎች ተወካዮች ጋር ዛሬ ተወያይተዋል ።በዉይይት መድረኩ ቀደም ሲል በስልጤ ዞን አሊቾ ዉሪሮ ወረዳ ዉስጥ ተከስቶ የነበረዉን አለመግባባት በብሔረሰቡ ባህላዊ እሴትና የእርቅ ስርዓት መሠረት በባህል ሽማግሌዎች አማከይነት እርቅ እንዳወርድ የተቀመጠዉ አቅጣጫ ተግባራዊ ተደርጎ አለመግባባቱ በተሳካ ሁኔታ እልባት ማግኘቱ ተገልጿል ።

በአካባቢዉ ተፈጥሮ የነበረዉን ጊዜያዊ አለመግባባት በመፍታት የአብሮነት መንፈሱ ወደቀድሞዉ መልካም ሁኔታ እንዲሸጋገር የባህል ሽማግሌዎቹ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር እንዳሻዉ ጣሰዉ ምስጋና አቅርበዋል ።

+2

Previous ከብሩህ ራዕይ ወደ ተጨበጠ የብርሃንምዕራፍ ስኬታማ የአምስት አመታት ጉዞዎች

Leave Your Comment

የቋንቋ አማራጭ

🇺🇸 English
🇪🇹 አማርኛ
🇪🇹 Afan Oromo