
ታህሳስ 18/2017(ወልቂጤ)
ከማዕከላዊ ኢትዮጵ ክልል የመጡ የብልጽግና ፓርቲ ሱፐርቪዥን ቡድን በወልቂጤ ከተማ አስተዳደር የፓርቲ እና የመንግስት ዋና ዋና የንቅናቄ ስራዎች አፈፃፀም ግምገማ አካሄደ።
ሱፐርቪዥን ቡድኑ በከተማ አስተዳደሩ በፓርቲ እና በመንግሥት የተሰሩ የልማት ስራዎች ምልከታ ያደረጉ ሲሆን በከተማ አስተዳደሩ የተጀመረው የኮሪደር ልማት የስራ እንቅስቃሴ ፣የጽዱ ከተሞች ለኢትዮጵያ ከፍታ ንቅናቄ አካል የሆነው በጉብርየ ቀበሌ የሞዴል የመፀዳጃ ቤት ግንባታ ጎብኝተዋል ።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር የብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ታደለ በቀለ እንደገለፁት በመንግሥትና በፓርቲ የሚከናወኑ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ውጤታማ እንዲሆኑ ጥንካሬዎችን እያስቀጠሉ ያጋጠሙ ችግሮችን የመፍትሔ ሀሳብ በማስቀመት በውጤት እየተገመገመ መምራት እንደሚገባ ገልጿል ።
የተጀመረው የኮሪደር ልማት ስራ፣አንድ ከተማ አንድ ፕሮጀክት በሚል የማህበረሰብ መድሀኒት ቤት ግንባታ በከተማ አስተዳደሩ በልዩ ትኩረት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ጠንካራ ግኑኝነት በመፍጠር ወደ ተግባር በመግባት ለማህበረሰቡ የግንዛቤ ስራ በመስራት በክትትልና ድጋፍ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ
ብለዋል።

በጉብርየ ቀበሌ የተገባው ዘመናዊ የማፀዳጃ ቤት ግንባታው ከ8 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ በመገንባት በአጭር ጊዜ መጠናቀቁ ለሌሎች የልማት ስራዎች አፈፃፀም ተሞክሮ እንደሚሆን አቶ ታደለ ተናግረዋል።
በከተማ አስተዳደሩ በመንግስት እና በህብረተሰቡ ተሳትፎ በጤና ፣በትምህርት እንዲሁም በተለያዩ ማህበራዊና በሌሎች ዘርፎች በርካታ ተግባራት የተከናወነው ሲሆን ቀጣይም በሚከናወኑ ተግባራት ግልፀኝነት እየተፈጠረ ሁሉም የድርሻውን መወጣት እንደለበት አስገንዝበዋል ።

በግምገማ መድረኩ በከተማ አስተዳደር በመንግስት እና በፓርቲ ከተከናወኑ ተግባራት መካከል በጤና ዘርፍ ፣በስራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍ፣ከገቢ ልማት፣የኑሮ ውድነትና ዋጋ ንረት ለማሻሻል የተከናወኑ ተግባራት ፣ከፀጥታ ደህንነት ሥራ፣የከተማ ልማት ስራዎች ፣የግብርና ልማት ስራዎች እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
በመጨረሻም ሁሉም አቅሙን አሟጦ በመጠቀም ለውጤት በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባ ተጠቁሞ ግምገማው ተጠናቋል።

