የከተማው ወቅታዊና ነባራዊ ሁኔታ እና የትራንስፎርሜሽን ተቋማት የማዘጋጃ ፣የገቢ፣ የስራ እድል ፈጠራና የግብርና ተቋማት የ2017 ዓ.ም የ5ወራት ተግባር አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ውይይት ተካሄደ።

ታህሳስ 3/2017ዓ.ም(ወልቂጤ)

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት በከተማው ወቅታዊ ሁኔታ እና የትራንስፎርሜሽን ተቋማት የ2017 ዓመተ ምህረት የ5ወራት እቅድ አፈፃፀም የምክክር መድረክ አካሄደ።

የከተማው ወቅታዊና ነባራዊ ሁኔታ እና የትራንስፎርሜሽን ተቋማት የማዘጋጃ ፣የገቢ፣ የስራ እድል ፈጠራና የግብርና ተቋማት የ2017 ዓ.ም የ5ወራት ተግባር አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ውይይት ተካሄደ።

የከተማ አስተዳደሩ ብልጽግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ታደለ በቀለ እንደተናገሩት ከተማዋ አሁን ያለችበት ወቅታዊና ነባራዊ ሁኔታ ተረድተን ሁላችንም በአለን እውቀትና አቅም ለሁለንተናዊ እድገትና ልማት በጋራ መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል።

በማህበረሰቡ የሚነሳው የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግር ለመፍታ የገቢ አቅማችንን ማሳደግ ስንችል በመሆኑ የገቢ አሰባሰብ ስርዓታችንን አጠናክረን በመሄድ የሚስተዋሉ ክፍቶችን እየፈተሽን ለአንድ አላማና ግብ ልንሰራ ይገባል ሲሉ አቶ ታደለ አስረድተዋል።

በህዝብና በመንግሥት ተሳትፎ ሊሰሩ ከታሰቡት የኮሪደር ልማት በከተማ አስተዳደሩ አራት አቅጣጫ እንደሚለማ ጠቁመው በመጀመሪያው ፌዝ 17km እና በሁለተኛው ፌዝ ደግሞ 8km እንደሚለማ ተናግረዋል።

አንድ ፕሮጀክት ለአንድ ከተማ በሚል በጉብርየ ክፍለ ከተማ ላይ የህዝብ መድሀኒት ቤት በማህበረሰቡ ተሳትፎ ለመገንባት የቦታ ዝግጀትና ዲዛይን የተጠናቀቀበት አግባብ መኖሩንም አንስተው ለዚህም ተግባር መሳካት የበኩላችንን ልንወጣ ይገባል ብለዋል።

አቶ ታደለ አያይዘውም የከተማችን ሰላምና የፀጥታ ጉዳይ ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ በመሆኑ ለጋራ ከተማችን ሰላም ዘብ በመሆን የከተማዋን መልካም ገፅታን በመገንባት የበኩላችንን ልንወጣ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የጤና ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሙባሪክ ዘይኑ እንደገለፁት እንደ ሀገር እየተሰራ ያለው የኮሪደር ልማት ስራ ወደ ከተማችን በመምጣቱ የማህበረሰቡን ችግር እንደሚፈታ ታምኖ ህዝባዊ መሰረት አስይዘን መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል።

አቶ ሙባሪክ አክለውም አሁን ካለው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ጋር ተያይዞ እየጨመረ የመጣው የኑሮ ውድነት ለማረጋጋት በከተማ ግብርና የተጀመሩ አበረታች ስራዎች ከተረጅነት ወደ ምርታማነት በመሸጋገር ማህበረሰባችን ተጠቃሚ እንዲሆን የማስቻል ተግባራት ማጠናከር ይገባል ብለዋል።

የከተማ አስተዳደሩ ብልጽግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ ወይዘሮ መንዚላት አህመድ እንደተናገሩት የኮሪደር ልማት ስራ ለከተማዋ መልካም ገፅታ በማሳደግ የከተማው ኢኮኖሚያዊ እድገት በማፋጠን ለነዋሪዎቿ በተለያዩ ዘርፎች ተጠቃሚ ለማድረግ ከፍተኛ ሚና እንዳለው አንስተዋል።

ወይዘሮ መንዚላ አክለውም በሥራ ዕድል ፈጠራ ጋር ተያይዞ በብድር አመላለስ፣ በደረጃ ሽግግር፣ ለወጣቱ የብድር አሰጣጥና የአንድ ማዕከላት ለኢንተርፕራይዞች ተገቢ ድጋፍ ላይ ሚታዩ ተግዳሮቶች እየለየን የቀጣይ የእቅድ አካል አድርገን ልንሰራበት ይገባል ብለዋል።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ የሆኑት አቶ ጴጥሮስ አስራት እንደገለጹት በከተማችን ማህበረሰብ የፀጥታ ስጋት የሆኑ አካባቢዎች በመለየት ከፀጥታ ሀይሉ ጋራ በቅንጅት መስራት ይገባናል ብለዋል።

አቶ ጴጥሮስ አክለውም ለወጣቶች ስራ እድል ለመፍጠር መንግስት ከሚበጅተው በጀት ባሻገር ቀድሞ የተሰራጩትን ብድሮች ተመላሽ በማድረግ እድሉን ላላገኙ ወጣቶች ስራ እድል ለመፍጠር ተመላሽ የሚሆንበትና ወጣቱ ተጠቃሚ የሚሆንበት አግባብ መፍጠር እንደሚገባ አስገንዝበዋል ።

በውይይት መድረኩም የከተማው ጠቅላላ አመራር፣ የቀበሌ ስራ አስኪያጆችና ሊቀመናብርት፣ የመሰረታዊ ፓርቲና ህዋስ አመራሮች ተሳትፈዋል።

Previous የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በሁሉም ዘርፍ የሚተገበሩ ስራዎች ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት የሚያስችሉ ሊሆኑ ይገባል – ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው

Leave Your Comment

የቋንቋ አማራጭ

🇺🇸 English
🇪🇹 አማርኛ
🇪🇹 Afan Oromo