ታህሳስ 1/2017 (ወልቂጤ)

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በዋና ዋና የንቅናቄ ተግባራት አፈጻጸም እና በቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ትኩረት ያደረገ የአመራር የምክክር መድረክ በሆሳዕና ከተማ እየተካሔደ ነው
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው በምክክር መድረኩ እንደገለጹት የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በክልሉ በሁሉም ዘርፍ የሚተገበሩ ስራዎች ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት የሚያስችሉ ሊሆኑ ይገባል ብለዋል።

ገቢ እና የስራ እድል ፈጠራ ለክልሉ ከምንም በላይ አስፈላጊ ዘርፎች ናቸው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ረገድ የተጀመሩ ስራዎችን ቀጣይነት ማረጋገጥ እንደሚገባም ርዕሰ መስተዳድሩ አመላክተዋል።
ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን ገቢ በሚፈለገው ልክ ማሰባሰብ ካልተቻለ ለማሳካት የታቀዱ ተግባራትን ውጤታማ ማድረግ አዳጋች ስለመሆኑም አብራርተዋል።
በሌላ መልኩ ለስራ እድል ፈጠራ የተለየ ትኩረት በመስጠት የዜጎችን ተጠቃሚነት ማሳደግ እንደሚገባም ርዕሰ መስተዳድሩ በንግግራቸዉ ጠቁመዋል።
በገቢ እና በስራ እድል ፈጠራ ላይ የተስተዋሉ ጥንካሬዎችን ማስቀጠል እና ያጋጠሙ ውስንነቶችን ፈጥኖ በማረም በዘርፉ የላቀ ውጤት ማስመዝገብ ይጠበቃል ብለዋል።
በክልሉ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገር የተጀመሩ ስራዎችን በዝርዝር በመፈተሽ ለውጤታማነቱ የጋራ ጥረት ማድረግ ተገቢ ስለመሆኑም ተናግረዋል።
ተረጂነትን ለማስወገድ የአመለካከት ለውጥ ማምጣት አብይ ጉዳይ መሆኑን የተናገሩት ርዕሰ መስተዳድሩ ለዚህም የሁሉንም አካላት የተቀናጀ ጥረት ይጠይቃል ሲሉም ጠቁመዋል።

በክልሉ ከተሞችን የማዘመን ስራ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ በተለይ የኮሪደር ልማት፣ አንድ ፕሮጀክት በአንድ ከተማ እና ሞዴል የህዝብ መጸዳጃ ቤቶች ግንባታን ያካትታል ብለዋል።
በክልሉ የሚሰጠውን አገልግሎት ውጤታማ ለማድረግ በሰባት ማዕከላት ላይ በ6 ቢሊየን ብር ወጪ የፊታችን ጥር ወር ላይ የቢሮ ግንባታ እንደሚጀመርም ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል።
የአመራር የአባላት ስልጠና እና የክልሉን አጠቃላይ ፖለቲካዊ ያለበትን ሁኔታ አስመልክቶ ምክክር እንደሚደረግም ጠቁመዋል።
በህዝብ አገልጋይነት ላይ የተስተዋሉ ጉድለቶችን በማረም ለተሻለ ለውጥ መስራት እንደሚገባም ርዕሰ መስተዳድሩ አሳስበዋል።

በመድረኩ በገቢ፣በስራ እድል ፈጠራና ኢንተር ፕራይዝ ፣ በአደጋ ስጋት እና የምግብ ዋስትና፣ በከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ዘርፎች ላይ የተከናወኑ ተግባራት የአፈጻጸም ሪፖርት እየቀረበ ነው።
በክልሉ የተከናወኑ ተግባራት በየሳምንቱ በክቡር ርዕሰ መስተዳድሩ አማካኝነት በተከታታይ ሲገመገሙ መቆየታቸው ይታወሳል።
መረጃው የማዕከላዊ ክልል መንግስት ኮ/ጉ/ቢሮ ነው

