ነሀሴ 2/2016ዓ.ም [ወልቂጤ ]

በወልቂጤ ከተማ አስተዳደር በክረምቱ መርሀ ግብር ለተማሪዎች እየተሰጠ ያለውን የተለያዩ ሞያ መስኮች ስልጠና አስመልክቶ ጉብኝት ተደረገ።
በተለያዩ ሙያ ዘርፎች ፍላጎታቸው መሰረት ያደረገ በመሰረታዊ በኮምፒውተር ክህሎት ስልጠና ፣በጋርመንትና በሶፍትዌር በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ለ550 ለሚሆኑ ተማሪዎች ለአንድ ወር ስልጠናው መሰጠቱን የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅህፈት ቤት ገለፀ።
በጉብኝቱ የወልቂጤ ከተማ ዋና የመንግስት ተጠሪ፣የከተማ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሀላፊ፣ የከተማ ወጣቶች ስፖርት ፅህፈት ቤት የወጣት ዘርፍ ተወካይ እንዲሁም ባለድርሻ አካላት የስልጠናን ማዕከላት ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

የወልቂጤ አስተዳደር ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ አብድልበር ሰኢድ እንደገለፁት በክረምቱ መርሀ ግብር ተማሪዎች ራሳቸውን በተለያዩ የሙያ ክህሎት እንዲያዳብሩና ጊዜያቸውን በአግባቡ ተጠቅመው የማህበረሰብ አገልግሎት ላይ እንዲሳተፉ እየተረገ ያለው ጥረት ከፍተኛ ነው ብለዋል።
አለም የደረሰበት የቴክኖሎጂ አቅም እኩል ለመራመድ ትውልድ ላይ በመስራት በእውቀትና በክህሎት የበቁ የነገ ሀገር ተረካቢ ዜጋ ለመፍጠር የተጀመሩ አበረታች እንቅስቃሴ ቀጣይነት እንዲኖረው ለማስቻል የሁሉም ባለድርሻ አካላት ተሳትፎ የሚጠይቅ ነው ሲሉ ተናግረዋል ።
እንደ መንግሥት የታቀደ የብልፅግና ጉዞ በሁሉም አግባብ እየተሳለጠ እንደሚገኝ የገለፁት አቶ አብድልበር ተተኪ ምርታና ምርታማነትን ማረጋገጥ እንደሚገባ ጠቁመዋል።
በዛሬ በተደረገው መልዕከታ ብዙ ተስፋ የሚጠበቁ ከዚህ በላይ አቅምና ችሎታ ያላቸው ተማሪዎች መኖራቸውን በጉብኙቱ መመልከታቸውን ገልፀዋል።

የወልቂጤ የከተማ አስተዳደር ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሀምዱ ካሚል እንደተናገሩት በቴክኖሎጂና በፈጠራ ስራ የሚታይ ውጤት ለማምጣት ትውልድ ላይ ትኩረት ሰጥተን በጋራ ልንሰራ ይገባል ብለዋል።
በክረምቱ መርሀ ግብር በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ለ550 ለሚሆኑ ተማሪዎች ስልጠና መሰጠቱን የገለፁ ሲሆን በዛሬው በተደረገው ምልከታ ተማሪዎች ከቁጥር በዘለለ በተግባር የስልጠናው ሂደት በምን አግባብ እየተከታተሉ እንደሚገኙ መመልከታቸውን ገልፀዋል።
ተማሪዎች ከሚያገኙት የክህሎት ስልጠና ባሻገር በክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ተሳታፊ በማድረግ የመማሪያ ቁሳቁስ እጥረት ላለባቸው ተማሪዎች ለመደገፍ እየተሰራ ያለው ሰብዓዊ አገልግሎት የመስጠት ስራም ከፍተኛ ነው ብለዋል።

የወልቂጤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሀላፊ አቶ ኸይሩ አህመዲን በኮሌጁ በተደረገው ምልከታ ላይ ተገኝተው እንደገለፁት ተማሪዎች በመረጡት የስልጠና መስክ ውጤት ያለው ተግባር እያከናወኑ እንደሚገኙ ተናግረዋል ።
ኮሌጁ እያደረገ ያለውን ድጋፍ በቀጣይም አጠናክሮ ተማሪዎች በበጋው ወቅት የትምህርት ሰዓታቸውን በማይሻማ መልኩ የሚያስፈልጋቸውን ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርግ ጠቁመዋል።

የወልቂጤ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽህፈት ቤት የወጣት ዘርፍ ተወካይ የሆኑት አቶ ዘመዴ በቀለ በጉብኝቱ ወቅት ተዘዋውረው በመተለከቱት ነገር መደሰታቸውን ገልፀው በክረምት በጎፈቃድ ተግባር ተማሪዎች ክህሎታቸው እንዲዳብር እየተሰራ ያለው ሥራ የሚያስደስት ነው ብለዋል።
ተማሪዎች በተለያዩ የፈጠራ ስራዎች ላይ ተሳታፊ በማድረግ ጊዜያቸውን በአግባቡ ተጠቅመው ውጤት የሚያስመዘግቡትና በሚፈልጉት ዘርፍ ብቁ እንዲሆኑ የማስቻል ስራ ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል ሲሉ ገልፀዋል።
የክረምቱ በጎ ፍቃድ አገልግሎት በሁሉም ዘርፍ እየተሰራ ያለው አበረታች ስራ ሁሉም ተሳታፊ በመሆን ሁላችንም ለመልካም ስራና ውጤት በጋራ ልንሰራ ይገባል ብለዋል።


ስልጠናው ሲሰጡ ያገኘናቸው መምህራን በበኩላቸው በክረምቱ መርሀ ግብር በተግባር የታገዘ ስልጠና ለተማሪዎች መሰጠቱ የሚበረታታና ለቀጣይም መሰል ተግባራት አጠናክሮ ከማስቀጠል አንፃር በአሁኑ የታዩ መልካም ነገሮችን በማስቀጠል ክፍተቶች ለይቶ በማውጣት ሊሰራበት እንደሚገባም አመላክተዋል ።

ስልጠናው እየተከታተሉ የሚገኙ ተማሪዎች በሰጡት አስተያየት በስልጠናው ወቅት ያገኙት እውቀት ቀላል እንዳልሆነ ገልፀው ጊዜያቸውን በተገቢው መጠቀም መቻላቸውን ተናግረዋል


All reactions:

