ችሎት ህብረተሰቡ የሚያነሳቸውን የመልካም አስተዳደር ችግሮች ከተገልጋዩ በቀጥታ ለአገልግሎት ሰጪ ተቋም በአንድ ማዕከል በተገኘበት ደረጃ በደረጃ እንዲሁም በአጭር፣ በመካከለኛና በረጅም ጊዜ የሚፈቱበት አግባብ እንደሚኖር ተናግረዋል።

ሐምሌ 25/2O16 ዓ/ም [ወልቂጤ]

የህበረተሰቡን የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት የከንቲባ ችሎት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተገለፀ።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ እንዳለ ስጦታው እንደገለፁት የከንቲባ ችሎት ህብረተሰቡ የሚያነሳቸውን የመልካም አስተዳደር ችግሮች ከተገልጋዩ በቀጥታ ለአገልግሎት ሰጪ ተቋም በአንድ ማዕከል በተገኘበት ደረጃ በደረጃ እንዲሁም በአጭር፣ በመካከለኛና በረጅም ጊዜ የሚፈቱበት አግባብ እንደሚኖር ተናግረዋል።

ህብረተሰቡ ሀሳቡን በነጻነት በመግለፅ የሚነሱ ቅሬታዎች እንደ ጉዳያቸው ይዘት ተገቢውን ምላሽ በመስጠት ዜጎች በመንግሥት ያላቸውን እምነት በመጨመር ህዝብ እና መንግስትን አቀራርቦ በቀጣይ መንግስት በሚሰራቸው ስራዎች ላይ ልማትን ለማሳለጥ ይረዳናል ብለዋል።

የከንቲባ ችሎት በሳምንት ሀሙስ ከጠዋቱ 3 ሰአት ተሰይሞ በፍርድ ቤት ያልተያዙ በአገልግሎት ሰጪ ተቋማት የሚፈቱ ጉዳዮች ተገቢውን መረጃዎች እንደ ማመልከቻና ቅጻ ቅጽ ይዘው በመቅረብ ጉዳያቸውን በአንድ ማዕከል የሚታይበት አግባብ ስላለ ሁሉም ባለጉዳይ ማህበረሰባችን በግልጸኝነት በቀጥታ ተገኝቶ ጥያቄውን በማቅረብ ምላሽ የሚያገኝበት አግባብ በመፈጠሩ ህብረተሰባችን ይህን ዘመናዊነት ተጠቅሞ ከተማችንን ማዘመን አለበት ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ችሎቱ የባለጉዳዮችን እንግልት በመቀነስ መንግስት ለህብረተሰቡ እርካታ በጊዜ ሰሌዳ እንዲሰራና የዘርፉን ጉዳዮች ጫና እንደሚቀንስ የወልቂጤ ማዘጋጃ ቤታዊ አስተዳደር ሀላፊ አቶ ይብጌታ ንዳ ተናግረዋል።

ሁሉም ባለድርሻ አካል በአንድ በተገኘበት ባለጉዳዩ ጥያቄውን በማቅረብ ውሳኔ የሚያገኝበትና ከፍተኛ የሆነ ጊዜንና ጉልበትን ቆጣቢ ሆኖ ትክክለኛውን ምላሽ በአንድ ማዕከል ላይ ለመስጠት ያስችላል ሲሉም ጠቁመዋል።

የልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ግርማ ንቅበሸዋ ችሎቱ በሃገሩቱ ባሉ ትልልቅ ከተሞች እየተተገበረ እንዳለ አውስተው ካለው ፋይዳ አኳያም ከነዚሁ ከተሞች ልምድ በመውሰድ የከንቲባ ችሎት እየተካሄደ እንደሚገኝ አብራርተዋል።

የከተማችን ፍርድ ቤት በተለያዩ የወንጀል ጉዳዮች ምርመራ ላይ ጊዜ የሚወስድ ስለሆነ ህብረተሰቡ በዚህ ችሎት በመገኘት ጥያቄዎቹንና ቅሬታዎቹን አቅርቦ ምላሽ ማግኘቱ ህዝቡ እርካታን ከማጎናጸፉም በላይ በመንግሥትና በህግ ላይ እምነቱን ያሳድራል ሲሉም የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ታሪኩ ዳግየ ገልጸዋል።

ከችሎቱ ተሳታፊዎች መካከል ከጉብሬ ክፍለ ከተማ የመጡት አቶ ክብሩ ሽርጋ እንደተናገሩት ትራንስፎርመር ተቃጥሎባቸው ለሚመለከተው አካል ቢያመለክቱም ምላሽ ባለማግኘታቸው ጥያቄያቸውን ለችሎቱ በማቅረብ ከፍተኛ እንግልታቸውን እንደቀነሰና ዘመናዊነት በተላበሰ መልኩ ምላሽ እንደተሰጣቸው ተናግረዋል።

የቤት ጥገና እንዲደረግላቸው ጥያቄያቸውን ይዘው የተገኙት የጤና ገራባ መንደር የጋራ መኖሪያ ቤት ነዋሪ በቀነ ቀጠሮ ጉዳያቸው እደሚፈታላቸው ምላሽ ማግኘታቸውን በመግለፅ የከንቲባ ችሎቱ ለባለጉዳይ የሚሰጠው እርካታ ከፍተኛ በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።

በችሎቱም የከተማው ከንቲባ የችሎቱ ሰብሳቢ፣ የማዘጋጃ ቤት ሀላፊ ምክትል ሰብሳቢ በመሆን እና የፐብሊክ ሰርቪስ ተወካይ ሀላፊፀሃፊ በመሆን ከህብረተሰቡ በቀጥታ የሚነሱ ጥያቄዎችን በመቀበል መድረኩን ተመርቷል።

Previous ከክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት አንዱ አካል የሆነው የችግኝ ተከላ መርሃግብር በሰላምበር ትምህርት ቤት ባለድርሻ አካላትን ባሳተፈ መልኩ ተካሄደ።

Leave Your Comment

የቋንቋ አማራጭ

🇺🇸 English
🇪🇹 አማርኛ
🇪🇹 Afan Oromo