ሐምሌ 23/2016ዓ.ም [ወልቂጤ]
ከክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት አንዱ አካል የሆነው የችግኝ ተከላ መርሃግብር በሰላምበር ትምህርት ቤት ባለድርሻ አካላትን ባሳተፈ መልኩ ተካሄደ።

የወልቂጤ ከተማ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽህፈት ቤት የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት አካል የሆነው የችግኝ ተከላ ና በርካታ ወጣቶችን የሚያሳትፉ የዲጂታል ክህሎት ፕሮግራሞች ከመሠረታዊ የኮምፒውተር ሥልጠና ጎን ለጎን እያስኬደ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡

የጉራጌ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ሃላፊ አቶ ደምስ ገብሬ በችግኝ ተካላው ላይ ተገኝተው እንዳሉት ከሁሉም የጉራጌ ዞን ወረዳዎች ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የተውጣጣችሁና ከትምህርት የመጣችሁ በዚህ በአረንጓዴ አሻራ ችግኞችን በመትከል ሂደት አሻራችሁን በማኖራችሁ ምስጋና ይገባችኋል።
የተለያዩ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ከባለድርሻ አካለት ጋር እየተቀናጀን እየሰራን ነው ለአብነትም ተማሪዎች በተለያዩ ዘርፍ ስልጠና እንዲያገኙ ማድረግ፣የትምህርት ቁሳቁሶች መሰብሰብ ፣አልባሳትን መሰብሰብ ፣ጧሪ ቀባሪ ያጡ አረጋዊያንን መደገፍናጀ መሰል ተግባሮች ላይ እየሰራን እንገኛለን።
ተማሪዎች ከቴክኖሎጂ ሥልጠና ባሻገር በጎነት እንዲማሩና ተረድተው እንዲሄዱ ለማስቻል ታስቦ የተዘጋጀ ኘሮግራም ነው መሰል ተግባሮችን በወረዳዎች አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ገልጸው።
በተጨማሪ የኢትዮጵያ ኮደርስ ከዩናይትድ አረብ ኤምሬትና ከኢትዮጲያ በጋራ ቀመሆን የሚሰጥ ዓለማቀፍ ሥልጠና አለ እንደ ዞናችን ለ37,000 የማህበረሰብ ክፍሎች ለስድስት ሳምንት የሚቆይ ሥልጠና ሲሆን በሶስት ኮርሶች የሚሰጥ መሆኑንም ጠቁመዋል።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የንግድ ገበያ ልማት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሙባሪክ ዘይኑ እንደገለፁት የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎትን በተመለከተ ከተማ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽህፈት ቤት በርካታ ተግባሮችን እያከናወነ እንደሚገኝ የሚታወቅ ነው ያሉ ሲሆን።
በርካታ የክረምት በጎፈቃድ ሥራዎች የተለያዩ ባድርሻ አካላትን በማሳተፋ እየሰራችሁ እንደምትገኙ የሚታወቅነው እኛም በሚያስፈልገው ሁሉ ከጎናችሁ ነን ችግኝ መትከል ብቻ ሳይሆን የፅድቀት መጠኑንምፀ መከታተል ተገቢ ነው ሲሉ አቶ ሙባሪክ ዘይኑ ገልጸዋል።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ሃምዱ ካሚል እንደገለፁት የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በ3 የስልጠና ማእከል እና በሶስት ዘርፎች 455 ተማሪዎች በመቀበል ከወልቂጤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅና ከትምህርት ጽህፈት ቤት በጋራ ስልጠና እየሰጠን እንገኛለን ያሉ ሲሆን፡፡

በተጨማሪም አዲስ ምዕራፍ የሚሆነው ታዳጊዎች አዳዲስ ክሂሎት እና ዕውቀቶችን እንደሚፈልጉ በመገንዘብ ፤ የወደፊቱን ጊዜ በተሻለ ለመጠቀም እንዲችሉ ለማድረግ
እንደ ሀገር የ “5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደርስ” ፕሮግራም አካል የሆነውን ስልጠና እንደ ከተማችን ደግሞ 4199 ኮደርስ በማመቻቸት ወጣቶች ተገቢው የዲጂታል ክህሎት እንዲኖራቸው ለማድረግ በቀጣይ
ስልጠና እንደሚሰጥ ገልጸዋል።

የማስጀመሪያ መርሀግብር ላይ ከዞን መዋቅር እና ከሁሉም የጉራጌ ዞኑ ወረዳ እና ከተማ አስተዳደር ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽህፈት ቤት ሀላፊዎች እንዲሁ ከተቋም የማኔጅመንት አካል እና ከክረምት የመሠረታዊ የኮምፒውተር ሰልጣኝ ተማሪዋች በጋራ የችግኝ ተከላ ኘሮግራም በሰላም በር አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አሻራቸው አኑረዋል ሲሉ አቶ ሃምዱ አብራርተዋል፡፡

የወልቂጤ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ተወካይ አቶ ደምስ ፈቀደ በበኩላቸው ይህ ተቋም ከትምህር ስራዎች ጋር በተገናኘ በርካ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ የሚታወስ ነው ያሉ ሲሆን በችግኝ ተከላውም ባደረገው አሳታፊነት አመስግነው ችግኝ ከመትከል ባሻገር መንከባከብ ተገቢ ነው ሲሉ አመላክተዋል።

የሰላምበር ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር አቶ ኑርጋ ገብሬ ለእንግዶች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ካስተላለፉ በኃላ ካሉ ትምህርት ቤቶች እኛን መርጣች የረንጓዴ አሻራችሁን በማሳረፋችሁ ምስጋና ይገባችኋል ያሉ ሲሆን ተቋሙ በትምህርት ዙሪያ እየሰራጀ ላለው ዘርፈ ብዙ ስራዎች እውቅና ሰጥተዋል ።

