የወልቂጤ ከተማ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅህፈት ቤት ሀላፊ ሀምዱ ካሚል ችግር ፈቺ ትዉልድ ለመፍጠር ታች ድረስ ወርደን በተማሪዎች ላይ በተለየ ትኩረትና ክትትል መስራት መቻል ይገባል ብለዋል።

ሐምሌ 3/2016ዓ.ም [ወልቂጤ ]

በክረምት መርሀ ግብር ለተማሪዎች መሰረታዊ የኮምፒውተር ስልጠና እንደሚሰጥ ወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅህፈት ቤት ገለፀ።

በወልቂጤ ከተማ አስተዳደር በሶስት ማዕከላት የወልቂጤ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ፣ያበሩስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህር ቤት እንዲሁም አባ ፍራንሷ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለአንድ ወር ለ700 ለሚሆኑ ተማሪዎች ስልጠናው እንደሚሰጥ ተገለፀ።

የጉራጌ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ሀላፊ አቶ ደምስ ገብሬ እንደገለፁት የአንድ ሀገር እድገትና ለውጥ ለማረጋገጥ በቴክኖሎጂ የታነፀ ትውልድ በማፍራት የሳይንስና የፈጠራ ስራዎች ላይ በትኩረት ልንሰራ ይገባል ብለዋል።

በጉራጌ በዞን በሳይንስና በፈጠራ ስራ በርካታ አቅም ያላቸው ተወዳዳሪ የሆኑ ተማሪዎች መኖራቸውን ገልፀው የነገ ሀገር ተረካቢ ትውልድ በመሆናቸው ከአለም እኩል መራመድ እንዲችሉ ተማሪዎች ያለው አጋጣሚና ሁኔታ በአግባቡ በመጠቀም እውቀት ማግኘት መቻል አለባቸው ሲሉ ገልፀዋል።

እንደ ዞን በዓምና ደረጃ 1200 ተማሪዎቹ በክረምቱ መሰረታዊ የኮምፒውተር ስልጠና የተሰጠ ሲሆን ጎን ለጎን በርካታ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ስራዎች መሰራታቸውን ተናግረዋል።

አቶ ደምስ አያይዘውም በዘንድሮ በክረምቱ መርሀ ግብር ከባለ ድርሻ ጋር በመተባበር የሚሰጠው የቴክሎጂ ስልጠና በተመረጡ ማዕከላት ስልጠናው በጥራት እንደሚሰጥ አንስተው ጎን ለጎን ተማሪዎች የበጎ ስራ ላይ በመሳተፍ የበኩላቸውን እንዲወጡ ጠቁመዋል።

የወልቂጤ ከተማ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅህፈት ቤት ሀላፊ ሀምዱ ካሚል ችግር ፈቺ ትዉልድ ለመፍጠር ታች ድረስ ወርደን በተማሪዎች ላይ በተለየ ትኩረትና ክትትል መስራት መቻል ይገባል ብለዋል።

በዚህ በክረምቱ መሰረታዊ የኮምፒውተር ስልጠና ከ700 በላይ ተማሪዎች የሚሳተፉበት ነው ያሉት አቶ ሀምዱ በከተማ አስተዳደሩ በሶስቱ ማዕከላት በተቀናጀ መልኩ ከተባባሪ አካላት ጋር የሚሰጥ ሲሆን ተማሪዎች ያላቸውን አቅምና ችሎታ የሚያውቁበት፣ እርስ እርስ ያላቸውን እውቀት የሚለዋወጡበት እንዲሁም የዞናችን በኢኖቬሽን በተለያዩ በፈጠራ ስራ ላይ የተሳተፉ ተማሪዎች ልምዳቸውን እያካፈሉ ትውልድ የምናበቃበት ትልቅ መርሀ ግብር ነው ሲሉ ገልፀዋል።

በክረምቱ የበጎ ስራ ተግባራት ላይ እንዲሳተፉ የማስቻል ስራ የሚሰራ ሲሆን ለማህበረሰባችን በተመረጡ አገልግሎቶች ተማሪዎች ማገዝና መሳተፍ በሚቹሉዋቸው በጎ ስራ ላይ የሚሳተፉ መሆኑን ገልፀው የወልቂጤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እያደረገ ያለው ድጋፍ ከፍተኛ ሲሆን በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ተማሪዎች ለማሰልጠን እንደ ተቋም እያደረገ ያለው ስራ የሚያስመሰግን ነው ብለዋል።

የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ሀላፊ አቶ ፈይሰል ሀሰን እንደተናገሩት ተማሪዎች በክረምቱ ወቅት ከአልባል ቦታ ራሳቸውን አርቀው እውቀትና ለውጥ የሚያመጡበት ነገር ምርጫቸው ማድረግ ይገባቸዋል ብለዋል።

በጎነት በአካባቢያችን ይጀምራል ያሉት አቶ ፈይሰል ሁላችንም የበኩላችንን በመወጣት በክረምት ከሚሰሩ የበጎ አገልግሎት ስራዎች ላይ ማለትም ለተቸገሩ ተማሪዎች የትምህርት መማሪያ ግብዓት፣ አልባሳት፣ አቅመ ደካማ የህብረተሰብ ክፍሎች ጥየቃና የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር በመሳተፍ በጎ ተግባር ላይ ሊሳተፉ ይገባል ሲሉ ገልፀዋል።

የወልቂጤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ኸይሩ አህመዲን እንደተናገሩት ሀገራችን እየገነባች ያለችው ዲጂታል ቴክኖሎጂ ለማሳደግ ሁሉም ሀላፊነት ወስዶ አቅምና ችሎታ ያላቸው ተማሪዎች ባለን አቅምና ሀብት ልንደግፋቸው ልናበረታታቸው ይገባናል ብለዋል።

የወልቂጤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለሳይንስና ቴክኖሎጂ ለተማሪዎች እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደ ሚቀጥል ገልፀው ከመሰረታዊ የኮምፒውተር ስልጠና በተጨማሪ በኮሌጁ የሚሰጡ የተለያዩ የሙያ ስልጠናዎችም ላይ እንደ ተማሪው ፍላጎትና ዝንባሌ በክረምቱ የስልጠና መርሀ ግብር እንደሚሰጥም ገልፀዋል።

በመጨረሻም የወልቂጤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ውስጥ እየተሰጡ የሚገኙ የተለያዩ ስልጠናዎች የመስክ ጉብኝት ተደርጓል ።

Previous በከተማ አስተዳደሩ የተሰሩ ልዩ ልዩ የልማት ስራዎች ከዞንና ከከተማ አስተዳደሩ በተውጣጡ አመራሮች በዛሬው እለት ተጎብኝቷል።

Leave Your Comment

የቋንቋ አማራጭ

🇺🇸 English
🇪🇹 አማርኛ
🇪🇹 Afan Oromo