ግንቦት 5/2016 [ወልቂጤ]
የህብረተሰቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት በከተማው በተለያዩ ዘርፎች የሚገኙ የአደረጃጀት ግንባር ማጠናከ እንደሚገባ የወልቂጤ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ገለፀ።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት በቼክ ሊስት በታገዘ የፓርቲ ተግባራት የሱፐርቪዥን ቡድን ሪፖርት ገመገመ።
በግምገማ መድረኩ በቀበሌዎች እና በተቋማት ላይ የተደረገውን የኢንስፔክሽን ስራ በማስመልከት በሱፐርቪዥን ተግባር የተሰማሩ አመራሮች ሪፖርት አቅርበው ሰፊ ውይይት ተካሂዷል ።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ አብድልበር ሰኢድ እንደገለፁት ባለፉት ወራት የተከናወኑ ተግባራት የአፈፃፀም ጉድለት እና ወደ ኋላ የተቀሩ ስራዎችን እየለየን ማህበረሰባችን የሚጠይቀውን የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት የሁሉም ባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ ተግባር ማጠናከር እንደሚገባ ገልፀዋል ።
ብልፅግና ፓርቲያችን የጀመራቸውን የልማት እና የብልፅግና ጉዞ ለማስቀጠል የአባላትና የፖለቲካ መሪው ንቁ ተሳትፎ ወሳኝ መሆን አለበት ሲሉ አቶ አብድልበር ሰኢድ ተናግረዋል ።
በተለያዩ ዘርፎች የሚገኙ የአደረጃጀት ግንባር ማጠናከ ይገባል ያሉት አቶ አብድልበር ሰኢድ አመራሩ የተሰጠውን ሀላፊነት በብቃትና በውጤት የከተማው ህዝብ እና ማህበረሰብ የሚመጥን ስራ መስራት እንደሚጠበቅበትም አስገንዝበዋል።
እንዲሁም በተግባር አፈፃፀም የነበሩ ድክመቶችና የተወሰዱ የመፍትሔ እርምጃዎችን የእየመረመርን የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ በማድረግ ለተሻለ ስራ እና ውጤት በእውቀትና በሳል አመራራዊ ስልት በመከተል መስራት ይገባል ሲሉ አቶ አብድልብር አብራርተዋል።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና ንግድ ገበያ ልማት ፅህፈት ቤት ሀላፊ የሆኑት አቶ ሙባሪክ ዘይኑ እንደተናገሩት ሁሉም አመራር ለአንድ አላማና ውጤት በጋራ በመቆም፣ በመግባባት እንዲሁም በመደጋገፍ የአንዱ ውጤት አጠቃላይ የአመራር እንደሆነ በመገንዘብ በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።

ወቅቱ የቴክኖሎጂ እና የመረጃ በመሆኑ በቀላሉ የህብረተሰቡን ችግር ፈቺ መሆን በሚችሉ የሚዲያ አውታሮች ለበጎ ነገር ተጠቅመን ጥሩ የመረጃ ልውውጥ በማድረግ ተቋማትም አገልግሎታቸውን ለማዘመን የፈጠራና ቴክኖሎጂ ስራ ላይ በንቃት ሊሳተፍበት ይገባል ብለዋል።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ አቶ ጴጥሮስ አስራት እንደተናገሩ የብልፅግና እሳቤ የሆነውን ስህተትን ማረምና ማስተካከል እንዲሁም መልካም የሆነውን በማስቀጠል ችግር ፈቺ አመራር መሆን እንደሚገባ አስገንዝበዋል ።
ለከተማችን ሁለንተናዊ እድገትና ለውጥ ለማስቀጠል ህዝቡ ከመንግሥት ጎን በመሆን እያሳየ ያለውን ድጋፍ በማስቀጠል ሁሉም በባለቤትነት በተሰጠው የሀላፊነት ቦታ ለእውነት ሊሰራ ይገባል ብለዋል።
እንዲሁም ለህዝቡ ጥቅም በንቃትና በውጤት የሚሰራ አመራር በማፍራት በሁሉም ቀበሌዎቻችን ጠንካራ አደረጃጀት መፍጠር አስፈላጊ ሲሆን በየቀበሌ የሚገጥሙንን የሀብት ውስንነቶች ለመቅረፍ የገቢ ምንጭ የምናገኝበት አማራጮችን አስፍተን ልንጠቀም ይገባል ብለዋል::

የወልቂጤ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ ወይዘሮ መንዚላ አህመድ እንደገለፁት ጠንካራ መሰረታዊ ፓርቲ አደረጃጀት በመፍጠር የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ መቻል አለብን ሲሉ ተናግረዋል ።
የእቅድ አፈፃፀማችንን እየገመገምን እና እየፈተሽን ከሪፖርት ባለፈ ለውጤት በመስራት ችግር ፈቺ አመራር በመሆን እርስ በእርሳችን ተሞክሮ እየወሰድን የምንማማርበት አግባብ መፍጠር መቻል አለብን ብለዋል።
በመጨረሻም በከተማ የተጀመሩ የልማት እና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ ህዝቡን በማሳተፍ ለውጤት መስራት እንደሚገባ በማመላከት በተደራጀ የልማት ሰራዊት ብልፅግና ማረጋገጥ እንደሚገባ ተጠቁሞ መድረኩ ተጠናቋል።
ሲል የዘገበው Wolkite City Administration Government Communication Affairs Office

