በወልቂጤ ከተማ በተማከለ የዲጂታል ቴክኖሎጂ መሰረት ልማት በመጠቀም የተቋማትና ከተማ አቀፍ የመረጃ ልውውጥ ውጤታማነት ለማሳደግ ለባለድርሻ አካላት የስልጠናና የውይይት መድረክ ተካሄደ።

ሚያዝያ 30/2016ዓ.ም[ወልቂጤ]

ለአንድ ሀገር እድገትና ሰላም ለማረጋገጥ ዘመኑ የሚጠይቅ እና የተማከለ የዲጂታል ቴክኖሎጂ በመጠቀም ፈጣንና ውጤታማ ስራ መስራት እንደሚገባ ተገለፀ።

በወልቂጤ ከተማ በተማከለ የዲጂታል ቴክኖሎጂ መሰረት ልማት በመጠቀም የተቋማትና ከተማ አቀፍ የመረጃ ልውውጥ ውጤታማነት ለማሳደግ ለባለድርሻ አካላት የስልጠናና የውይይት መድረክ ተካሄደ።

በመድረኩ የሀንኤል ሶፍትዌር ኢንጅነሪንግ ለጉራጌ ዞን ለወልቂጤ ከተማ የወንጀል መከላከልና መቆጣጠር ስራዎች ለማቀላጠፍ ሆቴሎች እና የአልጋ አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች ከዚህ በፊት ሲጠቀሙበት የነበረውን ማንዋል ወደ ዲጂታል በመቀየር አገልግሎት ላይ እንዲውል ማበልፀግ መቻሉ ተገልጿል ።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ እንዳለ ስጦታው እንደገለፁት የሀንኤል ሶፍትዌር ኢንጅነሪንግ ለሰራው ስራ በከተማ አስተዳደሩ ስም አመስግነው ለአንድ ሀገር እድገት እና ሰላም ለማረጋገጥ ወቅቱና ዘመኑ የሚጠይቅ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ መሆን ይገባል ሲሉ ተናግረዋል ።

ከተማችን በማዘመን የፀጥታና ደህንነት ስራ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ኋላ ቀር አሰራር በመቀየር ፈጣንና ውጤታማ ስራ መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል።

የሀንኤል ሶፍትዌር ኢንጅነሪንግ የበለፀገው ሶፍትዌር ጊዜና ጉልበት በመቆጠብ ፣ ወጪ በመቀነስ ፈጣን ምላሽ በመስጠት ለሰላምና ለፀጥታ ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው ብለዋል።

የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራ ማሳለጥ የሚቻለው የከተማውን ሰላምና ፀጥታ በዘላቂነት ማረጋጋጥ ሲቻል በመሆኑ ወንጀልን የመከላከል ስራዎች በቴክኖሎጂ እና በፈጠራ ስራዎች ታግዘን የምንሰራበት አሰራር ዘርግተን ሁለም ለተግባራዊነቱ መሳካት ርብርብ ሊያደርግ ይገባል ሲሉ አስገንዝበዋል ።

እንዲሁም ክቡር ከንቲባው አያይዘውም የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ዌብሳይት በአግባቡ ለከተማችን ሁለንተናዊ እድገት እና ብልፅግና በእውቀትና በብልሃት ዌብሳይቱ ጥቅም ላይ በማዋል ከተማችንን ለአለም የምናሳይበት መሆን መቻል አለበትም ብለዋል።

የሀንኤል ሶፍትዌር ኢንጅነሪንግ ባለቤት የሆኑት አቶ ብሩክ አበበ እንደተናገሩት የበለፀገው ሶፍትዌር ለጉራጌ ዞንና በከተማ ላይ የሚፈጠሩ ወንጀሎች ለመከላከል ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ሲሆን ከዚህ በፊት የነበረውን የእንግዶች መቀበያ ቅፅ ወደ ዲጅታል በመቀየርና በፎቶ ስካን በቀላሉ ወንጀለኛውን ለፖሊስ መረጃ እንዲደርስ ተደርጎ የተሰራ መሆንም ገልፀዋል።

እንዲሁም የከተማው የህዝብ ፍሰት በመመዝገብ ለጉብኝት ፣ለትምህርት ወቅቱን በመለየት መረጃ በመሰብሰብ ከፍተኛ የህዝብ ፍሰት በሚኖርበት ወቅት ቅድመ ዝግጅት ሪፖርት በማድረግ እገዛ እንዳለው ተናግረዋል።

አቶ ብሩኩ አያይዘውም የበለፀገው ሶፍትዌር በኢንሳ መመዘኛ ፍቃድ አግኝቶ ደህንነቱ የተጠበቀና ከተፈቀደው የፀጥታ አካል ውጭ የማግኘትና ማየት የማይችል መሆንና ከፍተኛ ሚስጥራዊ አሰራርን ተከትሎ የተሰራ ቴክኖሎጂ መሆኑንም አስገንዝበዋል ።

በምክክር መድረኩ የተገኙት የጉራጌ ዞን ሳይንስና ቴክኖሎጂ መምሪያ ሀላፊ አቶ ደምስ ገብሬ እንደተናገሩት ለዞናችን እድገትና ለውጥ ሁሉም በቁርጠኝነት በባለቤትነት በቅንጅት መስራት ሲቻል በመሆኑ የሚመጡ የቴክኖሎጂ ፈጠራዎች ጥቅማቸውን ተገንዝበን ወደ ተግባር መቀየር ስንችል ነው ብለዋል።

ተቋማት በቴክኖሎጂ ለመታገዝ ያሉበትን አቋም በመገንዘብ እና ችግሮቻቸውን በመለየት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ተቀራርበው ሊሰሩ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ሳይንስና ቴክኖሎጂ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሀምዱ ካሚል በበኩላቸው በቴክኖሎጂ መሰረት ያደረገ ስራ መስራት ፈጣንና ሁሉም ማህበረሰብ ተጠቃሚ የሚያደርግ እንዲሁም በቀላሉ ተደራሽነትን ለማሳደግ ያለው ጠቀሜታ ከፍተኛ ነው ብለዋል።

ወቅቱ የቴክኖሎጂ በመሆኑ ትኩረት ሰጥተን አጠገባችን ያሉትን የፈጠራ ስራዎች እያበረታታን እንደ ተቋማት ትኩረት የምንሰጣቸው የሀብት ብክነቶች በመከላከል ሁሉም በሀላፊነት በማገዝ ውጤት ያለው ስራ ልንሰራ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።

በውይይት የተሳተፉ አካላት እንደተናገሩት የከተማችን ሰላም ለማስጠበቅ እና ያሉብንን ስጋቶች ለመሻገር የሚያስችል በቴክኖሎጂ የተደገፈ ሶፍትዌር ከተማችን ላይ ለአገልግሎት መቅረቡ ከተማ አስተዳደሩን አመስግነዋል።

አያይዘውም ሁላችንም ለከተማችን ሰላምና ፀጥታ በዘላቂነት ለመፍታት እየተሰራ ያለውን መልካም ተግባር ከመንግሥት ጎን በመሆን የሚጠበቅባቸውን ስራ እንደሚሰሩም ተናግረዋል።

ቴክኖሎጂ መጠቀም ውዴታ ሳይሆን ግዴታ በመሆኑ የእለት ተለት ኑሮዋችን መጠቀም ስላለብን ዘመኑ የሚጠይቀውን ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ በመሆን ለስራው መሳካት የበኩላችንን መወጣት አለብን ብለዋል።

Previous የወልቂጤ ከተማ የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ለማሻሻል በትኩረት እየተሰራ መሆኑን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስትየውሃ፣ መስኖናማዕድንልማት ቢሮ አስታወቀ።

Leave Your Comment

የቋንቋ አማራጭ

🇺🇸 English
🇪🇹 አማርኛ
🇪🇹 Afan Oromo