“የጉራጌ ማህበረሰብ የለውጡን መንግስት በቃል ሳይሆን በተግባር የደገፈ ህዝብ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ ገለጹ

ሚያዚያ 12/2016

“የጉራጌ ማህበረሰብ የለውጡን መንግስት በቃል ሳይሆን በተግባር የደገፈ ህዝብ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ ገለጹ

የለውጡን መንግስት የሚደግፍ ህዝባዊ መድረክ ጠቅላይ ሚኒሰትር ዶ/ር አብይ አህመድ በተገኙበት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወልቂጤ ከተማ ተካሂዷል።

በመድረኩ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ እንደገለፁት “የጉራጌ ማህበረሰብ የለውጡን መንግስት በቃል ሳይሆን በተግባር የደገፈ ህዝብ ነው ብለዋል።

ለሀገር ኢኮኖሚ ዋልታና ማገር የሆነ ህዝብ ነው።

የጉራጌ ማህበረሰብ በተሰማራበት የሥራ አካባቢ ቤተሰብ መስርቶ እያለማና እየለማ የሚኖር ሀገር ወዳድ ህዝብ ነው ያሉት አቶ ላጫ በስራ የሚያምን፣ ተራማጅ፣ ተግባቢ፣ የወንድምና እህት ባህልን አክብሮ የሚኖር ህዝብ ነው ሲሉም ዋና አስተዳዳሪው ገልፀውታል።

የጉራጌ ማህበረሰብ ይቻላልን በተግባር ያረጋገጠ፣ መረዳደትን ባህሉ ያደረገ ህዝብ መሆኑንም አቶ ላጫ ጠቅሰዋል።

ማህበረሰቡ የአኩሪ ባህልና ዕሴት ባለቤት መሆኑን የጠቆሙት አቶ ላጫ መንግስት ያስጀመረውን የአረንጓዴ አሻራ ንቅናቄ በጉራጌ ባህላዊ የምህንድስና ጥበብ ጆፎሮን በየመንደሩ በማስፋፋት ፅዱና ማራኪ አካባቢን በመፍጠር ረገድ ጉልህ ድርሻውን በመወጣት ላይ ይገኛልም ብለዋል።

ጉራጌ ስራ መፍጠርን ባህሉ ያደረገ በንግድ፣ ዕቁብ፣ እድርና መሰል ተግባራትን መገለጫዎቹ ያደረገ ትልቅ ህዝብ መሆኑንም አቶ ላጫ ተናግረዋል።

Previous የሀገር ሰላምና ልማት ለማረጋገጥ የጉራጌ ዞን ወጣቶች እያደረጉት ያለው ንቁ ተሳትፎ አጠናክረው እንዲያስቀጥሉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ እንዳሻው ጣሰው ገለጹ።

Leave Your Comment

የቋንቋ አማራጭ

🇺🇸 English
🇪🇹 አማርኛ
🇪🇹 Afan Oromo