ሚያዝያ 9/2016ዓ.ም[ወልቂጤ]

በሳይንስና ቴክኖሎጂ ምርምርና ፈጠራ የዳበረ ትውልድ ለሀገር ግንባታ ጉልህ ሚና እንዳለው ተገለፀ።

“የሚሞክሩት ስናበረታታ የሚችሉትን እንፈጥራለን” በሚል መሪ-ቃል የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽህፈት ቤት 3ተኛ ዙር የሳይንስና ፈጠራ ውድድር በያበሩስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በድምቀት አካሄደ።

ተማሪዎች ወጣት ሀይል እንደመሆናቸው መጠን አልባሌ ቦታዎች ከመዋል ይልቅ በአገኙት አጋጣሚ የተለያዩ የፈጠራ ስራዎች ሙከራ ቢያደርጉ ነገ የተሻለ እንደሚሆንላቸው ተገልጿል።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ሃምዱ ካሚል እንደገለፁት “የሚሞክሩት ስናበረታታ የሚችሉትን እንፈጥራለን” የሚለውን መሪቃል ከግምት በማስገባት ለሚወዳደሩ ተማሪዎች በተቋሙ ድጋፍና ክትትል እንደሚደረግላቸው ገልፀው።

ህብረተሰቡ ወስጥ ለሳይንስና ፈጠራ ስራዎች ፋላጎትና ዝንባሌ ያላቸውን የህብረተሰብ ክፋሎች ለመድረስና ፍላጎታቸውን ለማሟላት የማህበረሰቡን ችግር ፈቺ የሆኑ የፈጠራ ስራና ሀሳቦች ሙከራዎች ፈልቀው ለምተውና ተሸጋግረው የማህበረሰቡ ችግር ፈቺ ደረጃ ላይ ለመድረስና

በቴክኖሎጂ ፈጠራ ሥራ የተፈጠረው መነሳሳት የፈጠራ ባለቤቶች ለማበረታታት እንዲሁም ተማሪዎች በሳይንስ ዘርፍ ያላቸውን የመማር ፋላጎት መቀነስ ለመከላከል የሳይንስና ፈጠራ ውድድሮችና ሽልማት ስነ-ስርዓት /ኤግዚቢሽን/ በማድረግ ለፈጠራ ስራዎችና ለፈጠራ ባለቤቶች እውቅና ለመስጠት ታልሞ የተዘጋጀ መሆኑን ሃላፊው ገልጸዋል።

የያበሩስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ምክትል ርዕሰ መምህር የሆኑት አቶ በቀለ በሀሩ በበኩላቸው የፈጠራ ስራና ኤግዚቢሽን ከዚህ ቀደም የተካሄደ ቢሆንም በዛን ጊዜ ያልተሳተፉ አካላት እንዲሳተፉ በማድረግ ኢንተርፕራይዞችና ኮሌጅ ያሳተፈ ውድድር መደረጉ የተሻለ ትውልድና የተሻለ ሥራ እንዲሰራ ይረዳል ያሉ ሲሆን።

የፈጠራ ስራ ዋና ዓላማው ትውልዱ የኢኖቬሽንና የምርምር አቅሙ የሚያሳድግበት እንደመሆኑ መጠን የእውቀት መነሻው ደሞ ትምህርት ቤት በመሆኑ ተማሪዎች የፈጠራ አቅማቸውን በአግባቡ እንዲጠቀሙ ትምህርት ቤቶች የበኩላቸውን ድጋፍ እያደረጉ ይገኛሉ ሲሉም ገልፀዋል።

አቶ ቀድር ሁሴን የወልቂጤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ኢንድስትሪ ኤክስቴንሽን ቴክኒክ ክህሎት አቅም ግንባታ ቡድን መሪ እንዳሉት ሀገራችን በቴክኖሎጂ ደረጃ ያለችበት ሁኔታ የሚታወቅ ሲሆን አቅማቸው የተፈተሹ የቴክኖሎጂ ስራዎች በማስፋት ማህበረሰብን ማስጠቀም መቻል አለብን ብለዋል።

አያይዘውም ወደ ዲጅታላይዜሽን ለመግባት የእኛም ኮሌጅ የተጣለበትን ግብ ለመወጣት በቴክኖሎጂና የተለያዩ ሶፍትዌሮች በመምህራን እየበለፀጉ ለሴክተር መስሪያ ቤቶች ለማሰራጨት ጥረት እየተደረገ ይገኛልም ብለዋል።

በእለቱም ውድድር የተሳተፉት ኢንተርፕራይዝ ዘርፍ፣ኮሌጅ ዘርፍና የግል ዘርፎች ተሳትፈውበታል።

በኤግዝቢሽኑ ኑሮን ሊያቀሉና ችግር ሊፈቱ የሚችሉ የፈጠራ ስራዎች ቀርበው ውድድር ተደረጎ አሸናፊ ለሆኑ የፈጠራ ስራ ባለቤቶች የማበረታቻ ሽልማትና ሰርተፍኬት ተበርክቶላቸዋል።

Previous ሚያዚያ 8/2016 ዓ/ም

Leave Your Comment

የቋንቋ አማራጭ

🇺🇸 English
🇪🇹 አማርኛ
🇪🇹 Afan Oromo