በወላይታ ሶዶ ከተማ እየተካሄደ ባለው የከተሞች ፎረም በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ በ12ኛ ክፍል ተማሪ የተሰራው ሮቦት ለእይታ ቀርቦ የበርካቶችን ቀልብ ስቧል።

የካቲት 13/2O16 ዓ/ም [ወልቂጤ]

በወላይታ ሶዶ ከተማ እየተካሄደ ባለው የከተሞች ፎረም በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ በ12ኛ ክፍል ተማሪ የተሰራው ሮቦት ለእይታ ቀርቦ የበርካቶችን ቀልብ ስቧል።

በመንግስት በኩል ድጋፍ ከተደረገ በርካታ የፈጠራ ስራዎችን ለመስራት ዕቅድ እንዳለውም ተማሪ ፍፁም ወርቁ ገልጿል።

ተማሪ ፍፁም ወርቁ የ12ኛ ክፍል ተማሪ ሲሆን በአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ሰዎችን ተክቶ የመስተንግዶ አገልግሎት የሚሰጡ ሮቦት መስራቱን ተናግሯል።

ሮቦቱ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ታግዘው የተሰራ መሆኑን የገለፀው ተማሪው በተለያዩ ቋንቋዎች ትዕዛዞችን እየተቀበላ የሚያስተናግድ መሆኑንም ተናግሯል።

በእንቅስቃሴ ወቅት ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን አልፎ አገልግሎት የሚሰጥ ስለመሆኑም ገልጿል።

ሮቦቱ እየተንቀሳቀሰ አገልግሎት ከመስጠቱም በተጨማሪ መንቀሳቀስ የማይችሉ አካል ጉዳተኞች አፕልኬሽን በመጠቀም ትዕዛዝ ሲሰጡ የሚቀበል እንደሆነም ተማሪው አስረድቷል።

ወጣቱ ከዚህ በተጨማሪም ለጤናና ግብርና ስራዎች አገልግሎት የሚውል የፈጠራ ስራዎችን ለመስራት ዕቅድ እንዳለው ተናግሯል።

በቅርቡ በድሬዳዋ በሚካሄደው ዓለም አቀፍ የፈጠራ ስራዎች ውድድር እንደሚሳተፍም ገልጿል ።

የወጣቱን የፈጠራ ስራ የጎበኙ አንዳንድ ግለሰቦች በበኩላቸው ባዩት ነገር እጅግ መደሰታቸውን ገልጸው መንግስት እንደዚህ አይነት የፈጠራ ስራ የሚሰሩትን ሊያበረታታ ይገባል ብለዋል።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሀምዱ ካሚል እንዳሉት እንደ ከተማው በፈጠራ ስራዎች ላይ የሚሳተፉ ግለሰቦችን መንግሰት እንደሚደግፍ አስረድተዋል ።

ተማሪ ፍፁም ወርቁ የጀመራቸው የፈጠራ ስራዎች ውጤታማ እንዲሆን ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግረዋ ።

Previous “ለ9ኛ ጊዜ የሚካሔደው የከተሞች ፎረም ዲጅታላይዜሽን ላይ ትኩረት ያደርጋል ተባለ”

5 Comments

  • mubarek
    February 21, 2024

    በጣም ገራሚ ነበር !! ፍፁም ከታገዘ ከከተማው አልፎ ለሀገሩም እንደሚጠቅም ሙሉ እምነት አለኝ፣
    በርታ!!!

  • Fikadu takineda
    February 22, 2024

    Bravo well done

Leave Your Comment

የቋንቋ አማራጭ

🇺🇸 English
🇪🇹 አማርኛ
🇪🇹 Afan Oromo