አቶ ሀምዱ ካሚል

1.የወልቂጤ ከተማ ሳይንስ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂራዕይ፣ተልዕኮ፣ዓላማዎችና ዕሴቶች

1.1. ተልዕኮ

  • በከተማው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ጉልህ አስተዋፅኦ የሚያደርጉ የሳይንስና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ስራዎችን ለህብረተሰቡ በአግባቡ በማልማት፣በመተግበርና በማስፋት ዞናዊ ብሎም አገራዊ የተወዳዳሪነት አቅምና በቴክኖሎጂ የዳበረ የአሰራር ስርዓት መፍጠር ነዉ፡፡

1.2. ራዕይ

  • “በ2030 በከተማና በክፍለ ከተማ ውጤታማ የሆኑ የሳይንስና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂዎችን በፍጥነት የመማር፣የማልማት፤የመፍጠር፣የማላመድ እና የመጠቀም አቅም ተገንብቶ ማየት”

 1.3. እሴቶች

  • በጎ ህሊናና ቅንልቦና፣
  • የስራ ፍቅር ናትጋት፣
  • ያልተገደ በአስተሳሰብና ምናባዊ ጉዞ፣
  • ለለውጥ በጋራ መስራት፤
  • ውጤታችንም ሆነ ውድቀታችን የጋራችን ነው፤
  • ችግርፈቺነት፤
  • የማይረካ የመማር ጥማት፤
  • ለትውልድ የሚተላለፍ መሠረት፣
  • ቀልጣፋና ውጤታማ አሰራርና ቀጣይነት ያለው መሻሻል፣

1.4. ጽ/ቤቱ  የተቋቋመበት ዓላማ

ጽ/ቤቱ የተሰጠውን ኃላፊነትና ተግባር ማለትም ዘመናዊ ጽ/ቤቱ የሆኑ ቴክኖሎጂዎችን በመመርመር፣በመቅዳት፣በማላመድና ያለዉን አቅም አሟጦ ለመጠቀም የሚያስችል የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የመዘርጋትና የማስፋፋት ሥራዎችን በስትራቴጂያዊ አስተሳሰብ ለመምራት፣በሁሉም ደረጃ ባሉ ፈጻሚዎች መካከል ተግባቦትን ፈጥሮ የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ የልማትና የለውጥ ዘመን ዕቅድ ያለውን ሥራዎችን ቴክኖሎጂያዊ ድጋፍ መስጠት ነዉ፡፡

 

 

2 Comments

  • Tamirat Tadesse
    February 18, 2024

    Ke software developer gar yeteyaze adis neger kale be page lay attach adrigulign

Leave Your Comment

የቋንቋ አማራጭ

🇺🇸 English
🇪🇹 አማርኛ
🇪🇹 Afan Oromo