
አቶ አብዶ ሰማን – የሥራና ክህሎት
ጽሕፈት ቤት ኃላፊ
የሥራና ክህሎት ጽ/ቤት ተልእኮ ራዕይ እና እሴት
ተልዕኮ
ምቹ የሆነ የኢንዱስትሪ ልማት መሰረት እንዲኖር የግል ባለሀብቱንና ኢንተርፕርነሩን ወደ ዘርፉ በማምጣት ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት፣ መዋቅራዊ ሽግግር በማፋጠን፣ የምርት ጥራትና ምርታማነትን በማሳደግ ገበያ መር ክህሎት ልማትና ትስስር ስራዎችን በማፋጠን ኢንዱስትሪዉ የመሪነት ሚና እንዲኖረዉ ማድረግ፣ ለዜጎች የስራ ዕድል መፍጠር፣
ራዕይ
ብቁ የሰው ሃብት ፤ምቹና አስተማማኝ የስራ እድል የሞላባት ኢትዮጵያን ማየት
ዓላማ
- ኢንተርፕራይዞችን በማስፋፋት መዋቅራዊ ሽግግር ማፋጠን ፤
- ወደ ዘርፉ የሚገቡ የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎችን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት መመልመል፣ ወደ ዘርፉ የሚገቡትን ማደራጀት እና እዉቅና እንዲያገኙ ማድረግ፡፡
- ኢንተርፕራይዞችን በማልማት ሰፊ የስራ ዕድል መፍጠር፣ሰፊ መሰረት ያለዉ ልማታዊ ባለሀብትና ኢንዱስትሪያሊስት እንዲስፋፉ ማድረግ
- ሰላማዊ የኢንደስትሪ ግንኙነትን፣ የማህበራዊ ምክክር ና የስራ ቦታ ትብብር ማስፈን
ዕሴቶች
- መብትና ግዴታውን የለየ የተሟላ ስብዕና ያለው የበቃ የሰው ሃይል
- ፍትሃዊ አሳታፊና ዲሞክራሲያዊ አመራር መለያችን ነው፣
- በማያቋርጥ ለውጥና መሻሻል እናምናለን!
- ኪራይ ሰብሳቢነትን እንፀየፋለን፣
- መረጃን ለልማት እናውላለን፣
- ተገልጋዮቻችን የሕልውናችን መሠረት ናቸው!
- ቅሬታ አቅራቢዎች መካሪዎቻችን ናቸው!
- የሴቶችን ፣የወጣቶችን እና አካልጉዳተኞችን ሁሉ አቀፍ ተሳትፎ እናረጋግጣለን!