

አቶ ተካልኝ አቡሌ
የወ/ከ/ስ/እ/ፈ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ተልእኮ ራዕይ እና እሴት
ተልዕኮ
ምቹ የሆነ የኢንዱስትሪ ልማት መሰረት እንዲኖር የግል ባለሀብቱንና ኢንተርፕርነሩን ወደ ዘርፉ በማምጣት ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት፣ መዋቅራዊ ሽግግር በማፋጠን፣ የምርት ጥራትና ምርታማነትን በማሳደግ ገበያ መር ክህሎት ልማትና ትስስር ስራዎችን በማፋጠን ኢንዱስትሪዉ የመሪነት ሚና እንዲኖረዉ ማድረግ፣ ለዜጎች የስራ ዕድል መፍጠር፣
ራዕይ
ብቁ የሰው ሃብት ፤ምቹና አስተማማኝ የስራ እድል የሞላባት ኢትዮጵያን ማየት
ዓላማ
- ኢንተርፕራይዞችን በማስፋፋት መዋቅራዊ ሽግግር ማፋጠን ፤
- ወደ ዘርፉ የሚገቡ የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎችን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት መመልመል፣ ወደ ዘርፉ የሚገቡትን ማደራጀት እና እዉቅና እንዲያገኙ ማድረግ፡፡
- ኢንተርፕራይዞችን በማልማት ሰፊ የስራ ዕድል መፍጠር፣ሰፊ መሰረት ያለዉ ልማታዊ ባለሀብትና ኢንዱስትሪያሊስት እንዲስፋፉ ማድረግ
- ሰላማዊ የኢንደስትሪ ግንኙነትን፣ የማህበራዊ ምክክር ና የስራ ቦታ ትብብር ማስፈን
ዕሴቶች
- መብትና ግዴታውን የለየ የተሟላ ስብዕና ያለው የበቃ የሰው ሃይል
- ፍትሃዊ አሳታፊና ዲሞክራሲያዊ አመራር መለያችን ነው፣
- በማያቋርጥ ለውጥና መሻሻል እናምናለን!
- ኪራይ ሰብሳቢነትን እንፀየፋለን፣
- መረጃን ለልማት እናውላለን፣
- ተገልጋዮቻችን የሕልውናችን መሠረት ናቸው!
- ቅሬታ አቅራቢዎች መካሪዎቻችን ናቸው!
- የሴቶችን ፣የወጣቶችን እና አካልጉዳተኞችን ሁሉ አቀፍ ተሳትፎ እናረጋግጣለን!
ግብ
- የቴክኒከና ሙያ ስልጠና ተደራሽነት፤ ፍትሃዊነትን ፤ጥራትና አግባብነት ማሳደግ
- የጥናትና ምርምር የማማከር አገልግሎት፤የቴክኖሎጂ አጠቃቀም፤ የተቋማዊ አቅምን ማሳደግ
- ዘላቂ የስራ እድል በመፍጠር የዜጎች ተታሚነትን ማሳደግ
- የስራ ገበያ መረጃ ስርዓት መዘርጋትና ተግባራዊ ማድረግ
- የጥቃቅን፤አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ሚና ማሳደግ
- የስራ እድል ፈጠራ አካታችነት ማረጋገጥ
- የስራ ሁኔታዎች ቁጥጥር በማስፋፋት የህግ ተፈፃሚነትን ማሳደግ
- የሙያ ደህንነትና ጤንነት አገልግሎት ማጠናከርና ማስፋፋት
- አዳዲስ ኢንተርፕራይዞችን በማቋቋም ነባር ኢንተርፕራይዞችን በማጠናከር ለዜጎች የሥራዕድል እንዲፈጠርና እና ኢንተርፕራይዞችን እንዲሸጋገሩ ማድረግ፡፡
- የኢንተርፕራይዞችን ልማትን ለማፋጠንና ከአካባቢ ብክለት የጸዳ የአምራች ኢንዱስትሪን ለማስፋፋት እንዲያግዝ ከዘርፍ ውጭ ለተሰማሩ ባለሀብቶች፣ ለዩኒቨርስቲ ምሩቃን እንዲሁም በአካባቢ ጥበቃ ዙሪያ ለኢንዱስትሪያሊስቶች ለዜጎች ግንዛቤ መፍጠር፡፡
- ኢንተርፕራይዞች ያሉባቸውን ክፍተቶቻቸውን ለመሙላት እንዲያግዝ የብር፣የማሽነሪዎች እና የሥራ ማስኬጃ ብድር እንዲመቻችላቸው ማድረግ፡፡
- ኢንተርፕራይዞች ያላቸውን የማምረቻና የመሸጫ ቦታ ክፈተት ለመሙላት የማምረቻና የመሸጫ ሼዶች በመገንባት ኢንተርፕራይዞች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ
- ኢንተርፕራይዞች በጥራት፣ በዋጋና በጊዜ በገበያ ላይ ተወዳዳሪ የሆነ ምርት እንዲያመርቱ እና ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎች በመኮረጅና በማሻሻል ኢንተርፕራይዞች እንዲሸጋገር ማድረግ፡፡
- የኢንተርፕራይዞች በገበያ ውስጥ ብቁ ተወዳዳሪ በመሆን ገቢ ምርቶችን በመተካትና በወጪ ምርቶች ላይ በአይነትና በብዛት እንዲያሳድጉ ለማስቻል ባዛርና ኤግዝብሽን በማዘጋጀት ኢንተርፕራይዞችን በማሳተፍ የሀገር ውስጥ ገበያ ትስስር መፍጠር፡፡