
የወልቂጤ ከተማ ከመዲናችን አዲስ አበባ በደቡብ ምእራብ 155 ኪ.ሜ፣ ከደቡብ ክልል ዋና ከተማ ሀዋሳ በስተሰሜን ምእራብ 430 ኪ.ሜ ከጅማ ከተማ ወልቂጤ 189 ኪ.ሜ፣ ከቡታጅራ ከተማ በስተሰሜን ምእራብ 9ዐ ኪ.ሜ እንዲሁም ከወሊሶ ከተማ በስተደቡብ 40 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ትገኛለች፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በዞኑ ካሉት ወረዳዎች ውስጥ የቸሃ፣ የአበሽጌና የቀቤና ወረዳ ያዋስኑዋታል፡፡
የከተማዋ ጠቅላላ የቆዳ ስፋት 7260 ሄ/ር ነው፡፡ በአሁን ወቅት ለተለያዩ የኢንቨስትመንት አገልግሎት ሊውል የሚችል መሬት በበቂ ሁኔታ ተዘጋጅታዋል ፡፡
የከተማው መሬት ክልል የወንዝ ተፋሰሶች ያለው ሲሆን የዋቤ እና የመጌቻ ወንዝ ተፋሰሶች ዓመቱን ሙሉ ያለማቋረጥ የሚፈሱ ወንዞች ሲሆኑ የመሬቱ አቀማመጥ ከ90% በላይ ሜዳማ ነው፡፡
ወልቂጤ በሃይማኖት መመዘኛ፣ የኦርቶዶክስ ክርስትያን፣ እስልምና፣ ፕሮቴስታንት፣ አምልኮ ማእከሎች አሏት። ብዙ ምግብ ቤቶች፣ ሲኖሩ ከብዙ ከተማዎች የተሻለ መስተንግዶ እንዳለ ብዙዎች ይናገራሉ። የአየርላንድ መንግስት ድጋፍ ደግሞ፣ የዞን መቀመጫ እና የህዝብ ቤተመጽሐፍት በዘጠናዎቹ መጨረሻ ገንብቶ የነበረ ቢሆንም፣ መጽሐፍ ቤቱን የከተማው ሁለተኛ ደረጃ ትምህርትቤት በቅርቡ ጠቅልሎት ህዝቡ ቤተ መጽሐፍ የሌለው ነው። ከተማው ላይ ከአዲስአበባ ሲገባ፣ የቤተመንግስት ሲገኝ፣ ትላልቅ መሪዎች ከተማዋን ሲጎበኙ ያርፉበት ነበር። አሁን ደግሞ፣ ወታደር እንደሰፈረበት ወይም ከተማው ጸጥታ ላይ ጉዳዮች ሲጭር፣ ወታደር መጥቶ ያርፍበታል እሚባል ነው። የመጠነኛ ት እይንተ ሜዳ (ስታዲየም) ሲኖር፣ የወልቂጤ ከተማ እግርኳስ ክለብ (ክትፎዎቹ) የቤት ሜዳውም ነው። ክለቡ፣ በ2012 አም. በኢትዮጵያ ዋና ማህበር (ሊግ) ለመጀመሪያ ጊዜ ተሳታፊ ለመሆን በቅቷል።
የወልቂጤ ከተማ በርካታ ብሄር ብሄረሰቦች ተፈቃቅረውና ተቻችለው የሚኖሩባት በዋነኛነትም የጉራጌ፣ የቀቤና እንዲሁም የሌሎች በርካታ ብሄሮች ብሄረሰቦች መናኸሪያ ናት፡፡ የህዝብ ቁጥሯም ከ122,517 ሺህ በላይ መሆኑ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ሚዲያ ተቋማት በከተማዋ የF.M አገልግሎት መስጫ ጣቢያ (F.M 89.2) ተገንብቶ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑ፣ ማንኛውም ጋዜጣ እና የህትመት ሚዲያ በየእለቱ ማግኘት የሚቻል መሆኑ፣ የኢ.ዜ.አ ቅርንጫፍ ማእከል መኖሩ፣ ከተለያዩ ቲቪ ማሰራጫ ጣቢያዎች በቀጥታ ተቀብሎ የሚያሰራጭ የመቀበያ እና የማሰራጫ ጣቢያ ተተክሎ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡
ሆቴልና ቱሪዝም ህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማት፣ ንግድ፣ ሪል ስቴት፣ ኢንዱስትሪ፣ አግሮ ኢንዱስትሪ፣ ከተማ ግብርና፣ ኮንስትራክሽን፣ በከተማው ስራ ላይ ያሉ ኢንቨስትመንቶች፣ ወልቂጤን ለኢንቨስትመንት ተመራጭ የሚያደርጓት ምክንያቶች፣ ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት መገኘቷ፣ የጊቤ ብሄራዊ ፓርክ በቅርብ ርቀት መገኘቱ፣ የግልገል ጊቤ ቁጥር 2 ፕሮጀክት ግንባታ በቅርብ ርቀት ላይ መገኘቱ፣ የመንግስት ዩኒቨርስቲ፣ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ፣ የግል ኮሌጆችና ሌሎች የማህበራዊ ተቋማት በከተማው ውስጥ መኖራቸው፣የተዘጋጀ 150 ሄ/ር ኢንዱስትሪያል ዞን መኖሩ፣ የለም መሬት ባለቤት መሆኗ፣ የሰው ኃይል እንደልብ መኖሩ፣ የኢኮኖሚና የኢንቨስትመንት ምቹ ፖሊሲዎች መነደፋቸውና ተግባራዊ መደረጋቸው፣ ለስራ ታታሪ ህዝብ ባለቤት መሆኗ ይታወቃል፡፡
© 2023 የድረገጹ መብት ለወልቂጤ ከተማ አስተዳደር የተጠበቀ ነው። | በሄክስ ላብስ የበለጸገ።